የግል መገናኛ ብዙሃን ፕሮፋይል

ዶይቸ ቬለ (DW) የጀርመን ዓለም አቀፍ ብሮድካስት

በኢትዮጵያ የውጭ ሀገር መገናኛ ብዙሃን / MIRH/ 07 ሰኔ  2015

በሳሙኤል አሰፋ

ዶይቸ ቬለ የጀርመን ዓለም አቀፍ የብሮድካስት ሚዲያ ሲሆን በኢትዮጵያ ከሚተላለፉ የውጭ ሀገር መገናኛ ብዙሃን መካከል አንዱ ነው፡፡ ዶይቸ ቬለ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰፊ ሥርጭትና ተደራሽነት ካላቸው መገናኛ ብዙሃን የሚመደብ ተቋም ነው። ጣቢያው በዓለም ዙሪያ በ32 ልዩ ልዩ ቋንቋዎች ሥርጭቱን ያስተላልፋል፡፡ የዶይቸ ቬለ ብሮድካስት ዘርፍ ዋና ዓላማ በተለያዩ ባህሎች እና ህዝቦች መካከል መግባባት እና የሃሳብ ልውውጥ ማዳበር እንደሆነ በድረ ገጹ ሰፍሯል፡፡ ዶይቸ ቬለ ከቴሌቪዥን እና ከሬዲዮ ሥርጭት በተጨማሪ በበይነ መረብ አማካኝነት የሚሰራጩ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የመልቲ ሚዲያ ይዘቶችን ያቀርባል፡፡ ጣቢያው ሥርጭት ካለው ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች መካከል ጥቂቶችን ለመጥቀስ ያህል ጀርመንኛ፣ እንግሊዝኛ፣ አረብኛ፣ ስፓኒሽ፣ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ እና በሌሎች ቋንቋዎች በልዩ ልዩ ማራጮች ይዘቶችን ያቀርባል። ለምሳሌ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተዘጋጅተው የሚቀርቡ የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን ሥርጭት አማካኝነት በዓለም ዙሪያ በኹሉም ሥፍራ ይደመጣል፡፡

ዶይቸ ቬለ እ.ኢ.አ መጋቢት 15 ቀን 1965 በኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሚዲያ የዜና አሠራጭ ሆኖ እንደተመዘገበ እና ሥርጭቱንም በአማርኛ እንደ ጀመረ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በመላው ኢትዮጵያ በአማርኛ ቋንቋ አገልግሎቱን በማስፋት በሚሊዮን የሚቆጠሩ አድማጮችን መድረስ ችሏል፡፡ የመጀመሪያው የአማርኛ ሥርጭት የ15 ደቂቃ ብቻ የነበረ ሲሆን በአሁን ወቅት ኦሮምኛና ትግርኛ ቋንቋን ጨምሮ በሳምንት ለሰባት ቀናት ያህል ኢትዮጵያ ውስጥ ይደመጣል፡፡

ዶይቸ ቬለ ከንጉሠ ነገሥት ኃይሌ ሥላሴ ጀምሮ እስከ አሁኑ ድረስ በዓለም፣ በአፍሪካ እና በኢትዮጵያ የተከናወኑ ሁነቶችን ለኢትዮጵያውያን አድማጮች በማድረስ ከ50 ዓመታት በላይ መዝለቅ ችሏል፡፡

የዶይቸ ቬለ ራዕይ

እ.ኤ.አ. በ 2025 ፣ DW ኢላማ ቡድኑን ከክልላዊ-ተዛማጅ እና ውይይትን በሚያበረታታ ተፈላጊ ይዘት የሚያበረታታ አስፈላጊ የዲጂታል መረጃ ምንጭ ሆኖ አቋሙን ማጠናከር ይፈልጋል። DW አካዳሚ የአውሮፓ ቀዳሚ የሚዲያ ልማት ተቋም ለመሆን መንገድ ላይ ነው።

ተደራሽነት

ዶይቸ ቬለ በአድማጮች ዘንድ ተወዳጅ ከሆኑ ዲጂታል መገናኛዎች መካከል ፌስቡክ፣ ዩቱዩብ እና ኢንስታግራም ይገኙበታል። በየሳምንቱ የDW ቪዲዮ ይዘት 225 ሚሊዮን ፣ በድምጽ 52 ሚሊዮን ተጠቃሚ ያለው ሲሆን የዲጂታል ጽሑፍ ገጾች 14 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች አሏቸው። በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2022 በበርካታ ሀገራት የይዘት ቁጥጥር ቢደረግበትም DW በሳምንት 291 ሚሊዮን ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን አድርጓል።

በዓለም አቀፍ የሳተላይት ኔትወርክ፣ በግምት ወደ 5,000 የሚጠጉ የአጋር ጣቢያዎች፣ በበይነ መረብ እና በተንቀሳቃሽ ስልክ ጭምር ይሰራጫል። የDW መተግበሪያ በተጠቃሚዎች ምርጫ መሰረት የመስመር ላይ ይዘትን ሲያቀርብ የሬዲዮ ሥርጭቶች በአፍሪካ እና በአንዳንድ የእስያ ክፍሎች ለሚገኙ አድማጮች በአስር ቋንቋዎች  ይሰራጫሉ፡፡ በጀርመን  የፌደራል የታክስ በጀት የሚደገፈው DW  በአለም ዙሪያ ከ4,000 በላይ ሠራተኞች ያሉት ሲሆን ከ140 በላይ ለሚሆኑ ብሄረሰቦች ሥርጭቱን ያደርሳል፡፡ ዶቸ ቬይለ  ብራስልስ፣ ዋሽንግተን ዲ.ሲ.፣ ለንደን፣ ቤሩት፣ ኪየቭ፣ ሞስኮ፣ ሌጎስ፣ ኬፕ ታውን፣ ናይሮቢ፣ ኒው ዴሊ፣ ታይፔ፣ ቦጎታ፣ ዋርሶ፣ እየሩሳሌም፣ ኢስታንቡል፣ ጃካርታ 16 ዓለም አቀፍ ቢሮዎች አሉት፡፡

 

ለበርካታ አመታት በአጭር ሞገድ SW ሬድዮ ለኢትዮጵያውያን አድማጮች ይተላለፍ የነበረው የጀርመን ድምጽ ራዲዮ፤ አማራጭ የመገናኛ ብዙሃን ባልተስፋፉባቸው በተለይ በወታደራዊ ደርግ እና በኢህአዴግ የመጀመሪያ አመታት ተአማኒ የመረጃ ምንጭ ሆኖ አገልግሏል፡፡ ከሌሎች ገለልተኛ የዜና አውታሮች መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ በነበረባቸው የግጭት፣ የጦርነት፣ የመፈንቅለ መንግስት፣ የድርቅ ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና ሌሎችም ወቅቶች በሌሎች ምንጮች መረጃ ማግኘት በማይቻልበት ሁኔታ ዋነኛ የመረጃ ምንጭ ሆኖ አገልግሏል፡፡

ምንጭ

https://www.dw.com

 

የሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ ማኅበረሰብ ሬድዮ

Previous article

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ሬድዮ

Next article

You may also like

Comments

Comments are closed.