ሕግ-ነክ

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ውሣኔዎች: ቅፅ 19

ሕግ-ነክ ሰነዶች/ MIRH/ 11 ሐምሌ 2014

ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

በተሻሻለው የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2/1/ ሥር የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሠበር ችሎት የሚሰጠው የህግ ትርጉም በየትኛውም ደረጃ ላይ በሚገኙ የፌደራል ወይም የክልል ፍርድ ቤቶች ላይ አስገዳጅነት ይኖረዋል ተብሎ መደንገጉ ፍርድ ቤቶች የሠበር ችሎቱ የሰጠውን የህግ ትርጉም ተከትለው በመስራት ለተመሳሳይ ጉዳዮች ተመሳሳይ ውሳኔዎች እንዲሰጡ ለማስቻል ነው፡፡

በሀገሪቱ ያሉ ፍርድ ቤቶች ለተመሳሳይ ጉዳዮች ተመሳሳይ ውሳኔዎችን መስጠት መቻላቸው የዳኝነት አገልግሎቱ ተገማች እንዲሆን ከማስቻሉም በላይ ባለጉዳዮችን ካልተገባ ወጭና ከእንግልት ሊያድናቸው እንደሚችልም ይታመናል፡፡ ይህን እውን ለማድረግ በተቻለ መጠን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች በአግባቡ ታትመው በመላው ሀገሪቱ ለሚገኙ ፍርድ ቤቶችና ለተለያዩ አካላት እንዲሁም ለህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሰራጩ ይደረጋል፡፡

በሌላ በኩል የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች በጥራዝ መልኩ መዘጋጀታቸው ጥናትና ምርምር ለሚካሄዱ የህግ ተመራማሪዎች፤ ለህግ ባለሙያዎች ለጠበቆች፣ ለምሁራንና በጠቅላላው ለህብረተሰቡ ውሳኔዎችን ተደራሽ ከማድረግ አኳያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑም ስለታመነበት ጭምር ነው፡፡

 

ዝርዝሩን ያንብቡ፡

የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ-19

 

የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ

Previous article

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ

Next article

You may also like

Comments

Leave a reply