ሕግ-ነክ ሰነዶች/ MIRH/ 12 ሐምሌ 2014
የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2/1/ ሥር የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከአምስት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የሚሠጠው የሕግ ትርጉም በየትኛውም ደረጃ ላይ በሚገኝ የፌደራል ወይም የክልል ፍርድ ቤት ላይ አስገዳጅነት ይኖረዋል ተብሎ በመደንገጉ ፍርድ ቤቶች የሰበር ችሎቱ የሰጠውን የሕግ ትርጉም ተከትለው እንዲሰሩ ለማስቻል ነው፡፡
በየፍርድ ቤቶች ለተመሳሳይ ጉዳዮች ይሰጥ የነበረውን የተለያዩ ውሳኔዎች በማስቀረት የፍርድ ቤቶች ውሳኔዎች ወጥነት እንዲኖራቸውና ተገማችም እንዲሆኑ ከማድረግ አኳያ ጠቀሜታው ከፍተኛ በመሆኑም ነው፡፡
በሌላ በኩል ውሳኔዎቹ በጥራዝ መልክ መዘጋጀታቸው ጥናትና ምርምር ለሚያካሂዱ የሕግ ተማሪዎችና ምሁራን፣ ለጠበቆችና ለሕብረተሰቡ በአጠቃላይ ውሳኔዎቹን በቀላሉ ለማግኘት ያስችላል፡፡
ዝርዝሩን ያንብቡ፡
federal-supreme-court-decisions-volume-5
Comments