ኢትዮጵያ ውስጥ የተዘጉ የኅትመት መገናኛ ብዙኃን
የተዘጉ የኅትመት መገናኛ ብዙሃን /MIRH/ 11 ሐምሌ2015 በፍቃዱ ዓለሙ እና በመቅደስ ምንአለ መግቢያ በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ አሻራ ካላቸው የሚዲያ ዘርፍ መካከል የኅትመት መገናኛ ብዙሃን ኹነኛ አስተዋጽዖ እንደነበራቸው መረጃዎች ይገልጻሉ፡፡ ይሁንና በአሁኑ ወቀት ዉጥራቸው እየመነመነ የመጣው የኅትመት መገናኛ ብዙሃን ከጥቂት ጋዜጦች (የመንግሥት) በስተቀር በልዩ ልዩ ምክንያት ብዙዎቹ የኅትመት ሚዲያዎች አንድም በወረቀት ኅትመት መወደድ አልያም የዲጅታል ሚዲያ ተጽእኖ መቋቋም ባለመቻላቸው እና በሌሎች ምክንያቶች ከገቢያ እንዲወጡ አስገድዷቸዋል፡፡ በዚህ እትም ከገቢያ የጠፉ ...