ዲላ ዩንቨርስቲ ማኅበረሰብ ሬዲዮ / MIRH/ 24 ሚያዚያ 2015
በመቅደስ ማንአለ
የዲላ ዩንቨርስቲ ማኅበረሰብ ኤፍ ኤም 89.0 ሬድዮ ጣቢያ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ እና አካባቢው አገልግሎት ለመስጠት በማሰብ ጥቅምት 15/2010 ዓ.ም ከሚመለከታው አካል ሕጋዊ ፈቃድ የወሰደ ሲሆን የሙከራ ሥርጭቱን የጀመረው መስከረም 6/2013 ዓ.ም ነው፡፡ ሆኖም ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቆ መደበኛ ሥርጭቱን የጀመረው ግንቦት 2013 ዓ.ም ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ሬዲዮ ጣቢያው ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ እና ለአካባቢው በቀን የአሥር ሰዓት ሥርጭት ይሰጣል፡፡
የማኅበረሰብ ሬድዮ ጣቢያው እንደ ጤና፣ ግብርና፣ ትምህርት፣ (በሴቶችና በአካል ጉዳተኞችና ሕፃናት ላይ የሚያተኩሩ አስተማሪና አዝናኝ መረጃዎችን ለአድማጮች በማድረስ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል፡፡
የዲላ ዩንቨርስቲ ማህበረሰብ ጣቢያ ባካሄደው የዳሰሳ ጥናትም የሥርጭት አድማሱ በጌድዮ ዞን በሲዳማ ክልል እና በማዕራብ ጉጂ ዞን በስፋት የሚደመጥ በአማሮና ቡርጂ ልዩ ወረዳወች፣ በጋሞ፣ በወላይታ፣ በካባታና በዳውሮ ዞኖችም በአብዛኛው በጥራት ይደመጣል፡፡
ይህን ሬድዮ ጣቢያ ለማስተዋወቅ በዩንቨርስቲው ማኅበራዊ ድረ-ገፅ እና በወላይታ ፋና ኤፍ ኤም 99.9 በማስተዋወቅ ጥረት ተደርጓል፡፡
የዲላ ዩንቨርስቲ ማኅበረሰብ ኤፍ ኤም 89.0 ሬድዮ ጣቢያ ለ25 ሰዎች የሥራ እድል በመፍጠር እና በከፍተኛ ደረጃ ተደራሽ በመሆን በጥራት ላይ ያተኮረ ሥራን በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡
Comments