ማህበረሰብ ተኮር መገናኛ ብዙሀን ፕሮፋይል

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ሬድዮ

ማኅበረሰብ ሬድዮ/MIRH/ 12 ሰኔ 2015

በመቅደስ ምንአለ

የደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ ኤፍ ኤም 97.7 ለማርቆስ እና ኣካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት ለመስጠት በደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመ ነው፡፡ ሐምሌ 2007 ዓ.ም ፍቃድ አግኝቶ ሰኔ 25/2008 ዓ.ም የሙከራ ሥርጭት ጀመረ፡፡ ጣቢያው ከኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለለሥልጣን ብሮድካስት አዋጅ ቁጥር 533/07 አንቀጽ 28 መሠረት በቁጥር 33/2007 ዓ.ም የማኅብረሰብ ሬድዮ ባለቤትነት ፍሪኩዌንሲ 97.7 ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡ በዚህ መሠረት ሐምሰሌ 2007 ዓ.ም ፍቃድ አግኝቶ ሰኔ 25/2008 ዓ.ም የሙከራ ሥርጭት ጀመረ፡፡

ሬድዩ ጣቢያው መደበኛ ፕሮግራሙን ሲጀምር በቀን ለስድስት ሰዓታት ያህል ነበር፡፡ በቅርቡ የሥርጭት አድማሱን በማራዘም ወደ አስራ አንድ ስዓት አሳድጓል፡፡ ከፍ በማድረግ የተለያዩ ሬዲዩ ጣቢያው በየቀኑ ከሚያቀርባቸው ዝግጅቶች መካከል ግብርና፣ ትምህርት፣ ጤና፣ የሴቶች እና የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ፣ የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የማኅበራዊ ጉዳዮች የምክክር መድረክ፣ ባህል እና ልዩ ተሰጥዖን የመሳሰሉት ናቸው፡፡

የደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ ምስራቅ ጎጃም በሚገኙ 10 ወረዳዎች፣ በምዕራብ ጎጃም 4 ወረዳዎች፣ በኦሮሚያ ክልል ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ደራ ወረዳ ድረስ በመረጃ ምንጭነት ያገለግላል፡፡

የሥራ እድል በተመለከተ ሬድዮ ጣቢያው ለ25 ሰዎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡ በተጨማሪም አሥር የበጎ ፈቃድ ሠራተኞች እንዳሉ ከጣቢው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ዓላማዎች፡-

  • የሬዲዮስርጭትን በመጠቀም በደብረ ማርቆስ ከተማ እና አካባቢው ያለውን የመረጃ ተደራሽነት ለማሳደግ እና በግብርና፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በንግድ እና ስራ ፈጣሪነት፣ በአካባቢ፣ በአየርንብረት ለውጥ፣ በሰው ሃይል ልማት ላይ ባሉ በርካታ ወሳኝ እና አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ።
  • የደብረማርቆስና አካባቢው ተማሪዎችን፣ አርሶ አደሮችን፣ መምህራንን እና ማሕበረሰቦችንትምህርታዊና ልማትን የሚያግዙ ዘመናዊ፣ ዲጂታል እና ሳተላይት የኤፍ ኤም ሬድዮ ኮሙዩኒኬሽን ግብአቶችን ማቅረብ።
  • በድምጽየሚቀርቡ ትምህርታዊ ዝግጅቶችን፣ የአካዳሚክ እንቅስቃሴዎችን እና የምርምር ውጤቶችን ለሁለቱም የዩኒቨርሲቲው ውስጣዊ እና ውጫዊ ማህበረሰብ ማቅረብ፡፡
  • የዩኒቨርሲቲተማሪዎችን እና የአካዳሚክ ሰራተኞችን እንዲሁም የአካባቢውን ህዝብ በትምህርት፣በመረጃዊ እና በመዝናኛ ፕሮግራሞች በማቅረብ ግብዛቤ መፍጠር፡፡
  • የአካባቢውንማህበረሰብ ባህል፣ ቋንቋ እና ሌሎች እሴቶችን ለመጠበቅ እና ማስተዋወቅ።

ዶይቸ ቬለ (DW) የጀርመን ዓለም አቀፍ ብሮድካስት

Previous article

የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በኢትዮጵያ Voice of America (VOA)

Next article

You may also like

Comments

Comments are closed.