ይማሩ

የዜና ጉዳይ መረጣ እና ምዘና 

ይማሩ /MIRH/ 17 ጥር  2022

በዴቪድ ብሪወር

 

በዜና የሚነሱ ርእሰ ጉዳዮች ባላቸዉ አንገብጋቢነትም ሆነ ተደራሾች በሚሰጡት ስሜት የተለያየ ነዉ፡፡ አንዳንድ ጉዳዮች ቀለል ያሉ እና ጥልቀት የሌላቸዉ ሲሆኑ እንደ እሳት ወይም የመኪና አደጋ መሰል ሁነቶችን ተመስርተዉ በቀላሉ የሚቀርቡ ይሆናሉ፡፡ የዚህ አይነት ጉዳዮች ዋና ዋና ነጥቦችን በማቅረብ ያለ ትንተና ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡

በሌላ በኩል አንዳንድ ጉዳዮች የጋዜጠኛዉ/ዋን ምርምር፣ ክትትል እና ድፍረት የሚጠይቁ እና ጠበቅ ያሉ በአቀራረባቸዉም ጠንከር ያሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የዚህ አይነት ጉዳዮች በዛ ያለ ጊዜ፣ ገንዘብ እና ትኩረት የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ወሰብሰብ ያሉ ጉዳዮችን በተሟላ ሁኔታ ለማቅረብ ጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡

ሁሉም ጉዳዮች እኩል ክብደት ስለሌላቸዉ እና ተመሳሳይ የጊዜ እና የጥረት መጠን ስለማይጠይቁ ጋዜጠኞች በጉዳዮች መካከል ያለዉን የክብደት ልዩነት በጥንቃቄ ሊመዝኑ ይገባል፡፡

የጉዳዮች ምዘና/ማወዳደር

ሶስት የጉዳይ አይነቶችን እናያለን፡፡

አንደኛዉ የጉዳይ አይነት እጅግ ወሳኝ የሆኑ እና በርካታ ተያያዥ ጉዳዮች ተካተዉባቸዉ በጥልቅ የሚዘገቡ ሲሆኑ ለመስተጋብር የሚመቹ የዲጂታል ግብዓቶችንም ያካትታሉ፡፡

ሁለተኛዉ የጉዳይ አይነት ጠቃሚ የሆነ እና በቂ የመረጃ ግብዓቶች ያሉት ሆኖ ተጨማሪ መስተጋብራዊ ዲጂታል ግብዓቶችን የሚፈልግ የጉዳይ አይነት ነዉ፡፡

ሶስተኛዉ የጉዳይ አይነት ጠቃሚ የሆነ ነገር ግን ቀለል ያለ እና የግድ የታዳሚዉን ተሳትፎ ወይም መስተጋብር የማይፈልግ ነዉ፡፡

የጉዳይ ምዘና ጠቀሜታዎች

ምንም እንኳን ከላይ የዘረዘርናቸዉ ሶስት የጉዳይ አይነቶች ብቸኛ የማወዳደሪያ መስፈርት ባይሆኑም እነዚህን መሰል ክፍልፋዮች ማዘጋጀቱ ለዜና ክፍሎች የራሱ የሆነ ጠቀሜታ አለዉ፡፡ ይህን ማድረግ ጋዜጠኞች የተለያዩ ጉዳዮች በገጠሟቸዉ ጊዜ ምን ያህል ግብዓቶች እንደሚያስፈልጓቸዉ በቀላሉ መመዘን እንዲችሉም ይረዳቸዋል፡፡ በተመሳሳይ አርታኢዎች ለዘጋቢ ጋዜጠኞች እያንዳንዱን ጉዳይ በምን ያህል የምርመራም ሆነ የአቅርቦት ጊዜ ማቅረብ እንዲሁም ምን አይነት ግብዓቶች ማስገባት እንዳለባቸዉ በማስረዳት የሚጠፋዉን ጊዜ እንዲቆጥቡ ይረዳል፡፡

የዜና ምዘና መስፈርቶቹን በዜና ክፍሉ ላሉ ባለሙያዎች እንዲዳረስ በማድረግ መግባባትን መፍጠር እና የዘገባ ሂደቱን ማቀላጠፍ ከማስቻሉም በላይ የዜና ክፍል ዉይይቶችን ግልፅ እና የበለጠ ዉጤታማ በማድረግ ጥራት ያላቸዉ ዘገባዎች ለማቅረብ ያግዛሉ፡፡

ቀጥሎ የተዘረዘሩት ሃሳቦች የዜና ምዘናን ጉዳይ የበለጠ የሚያብራሩ ሲሆን እንደየመገናኛ ብዙሃኑ ምርጫ (በተለይም በቴክኖሎጂ ቅንጅት ለሚሰሩ የዜና ክፍሎች) ቅድሚያ እና ክብደት የሚሰጣቸዉ ጉዳዮች ሊለያዩ ይችላሉ፡፡

አይነት አንድ፡ እጅግ ወሳኝ የሆኑ እና በርካታ ተያያዥ ጉዳዮች ተካተዉባቸዉ በጥልቅ የሚዘገቡ፣ የዲጂታል ግብዓቶችን ያካተቱ ጉዳዮች፡፡

የዚህ አይነት ጉዳዮች በተደራሾች በጣም የሚፈለጉና አዲስ መረጃ የያዙ ሰበር ጉዳዮች ናቸዉ፡፡ ተደራሾች በአንድ አንገብጋቢ ጉዳይ ዙሪያ የተፈጠሩ አዳዲስ ነገሮችን ወይም የሚነገሩ አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የሚያምኗቸዉን እና የሚመርጧቸዉን አዉታሮች በቀን ዉስጥ በተደጋጋሚ እንዲከታተሉ የሚያደርጉ ጉዳዮች ናቸዉ፡፡ እነዚህ ጉዳዮች በተደራሾች እለታዊም ሆነ ዘላቂ ህይወት ላይ አንድ አይነት ተፅእኖ ያላቸዉ በመሆኑ እነዚህን መሰል ጉዳዮች ለመዘገብ በቂ ገንዘብ፣ ጊዜ እና የሰዉ ሃይል መመደብ ከመገናኛ ብዙሃኑ ይጠበቃል፡፡

ከጉዳዮቹ ዉስብስብነት እና አንገብጋቢነት አንፃር የሚካተቱ ተንቀሳቃሽ ምስሎች፣ እንደግራፊክስ ያሉ ግብዓቶች፣ አስረጂዎች፣ የምስል ስብስቦች፣ የጎዳና ላይ ቃለ መጠይቆች እና ሌሎች ተጨማሪ ግብዓቶች ከማስፈለጋቸዉም በላይ በማህበራዊ ድረ-ገፆች ለሚኖሩ ዉይይቶች እና ዘገባዎች ዝግጁ የሆነ የማህበራዊ ድረ-ገፅ ቁጥጥር ቡድን ያስፈልጋል፡፡ ይህን በምናደርግ ጊዜ ሌሎች ቀለል ያሉ ጉዳዮች ወደኋላ ሊቀሩ፣ እንደአስፈላጊነቱ ደግሞ ከዘገባ ሊሰረዙ ይችላሉ፡፡ ጉዳዮችን በምዘና መምረጥ አርታኢዎች መሰል ዉሳኔዎችን በቀላሉ ለመወሰን እንዲችሉ ያደርጋል፡፡

አይነት ሁለት፡ ጠቃሚ የሆነ እና በቂ የመረጃ ግብዓቶች ያሉት ሆኖ ተጨማሪ መስተጋብራዊ ዲጂታል ግብዓቶችን የሚፈልግ የጉዳይ አይነት፡፡

የዚህ አይነት ጉዳዮች ምንም እንኳን ጠቃሚ ቢሆኑም ጥቂት ምንጮች ብቻ ተካተዉባቸዉ በቀላሉ የሚቀርቡ እና ዲጂታል ግብዓቶችን በተጨማሪነት የሚፈልጉ ናቸዉ፡፡ በቴሌቪዥን ሲቀርቡ አጭር የአየር ሰዓት የሚወስዱ፣ ምናልባትም በሁለት የምስል ገፆች ብቻ የሚጠናቀቁ እና ግራፊክስ አጋዦች በማካተት የሚዳብሩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ጉዳዮች የበለጠ ለማዳበር ሲባል የማህበራዊ ትስስር ድረ-ገፆች ላይ የሰፈሩ አስተያየቶችን ማካተት እና የተደራሾችን ድምፅ ማንፀባረቅ ይቻላል፡፡

ይሄኛዉ የጉዳይ አይነት በአይነት አንድ ካየነዉ የጉዳይ አይነት የተለየ ሲሆን ዘገባዎቹን አጠናክሮ ለማቅረብ የሚወስደዉ ጊዜም አጠር ያለ ነዉ፡፡

አይነት ሶስት፡ ጠቃሚ የሆነ ነገር ግን ቀለል ያለ እና የግድ የታዳሚዉን ተሳትፎ ወይም መስተጋብር የማይፈልግ የጉዳይ አይነት ነው፡፡

እነዚህ የጉዳይ አይነቶች ብዙ ምርምር የማይፈልጉ እና በቀላሉ መሰረታዊ መረጃዎችን በማካተት የሚቀርቡ ናቸዉ፡፡

በጋዜጠኛዉ ቃለ ዜና ብቻ ወይም አንድ ምስል ብቻ በማካተት የሚቀርቡ የቴሌቪዝን ዘገባዎች ለእዚህ ምሳሌ የሚሆኑ ሲሆን የዚህ አይነት ጉዳዮች ለማዘጋጀት አጭር ጊዜ የሚወስዱ ናቸዉ፡፡

በአንድ የዜና ክፍል ዉስጥ አርታኢዎች ዋና ዋና ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ ዘገባዎችን እንዴት ሊመርጡ እንደሚችሉ የሚያሳይ ሞዴል በቀላሉ በመቅረፅ በዜና ክፍሉ ዉስጥ የሚሰሩ ማናቸዉም ሰዎች የዜና ክፍሉን የጉዳይ ምዘና ዝንባሌ በቀላሉ እንዲረዱት ማድረግ ይችላሉ፡፡

 

ለተጨማሪ ንባብ:

Story weighting system for breaking news

ተፈላጊ ጋዜጠኞች እንዴት ያሉ ናቸዉ? ቀጣሪዎች ምን ይፈልጋሉ?

Previous article

ሥርዓተ-ጾታን ያገናዘበ የግጭት አዘጋገብ መመሪያ ለመገናኛ ብዙኅን

Next article

You may also like

Comments

Leave a reply