ሕግ-ነክ ሰነዶች/ MIRH/ 12 ሐምሌ 2014
ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት እና ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር የተጣጣመና መርሆቻቸውንና እሴቶቻቸውን ለማስፈጸም የሚያስችል ዘመናዊ የወንጀል ፍትህ ሂደት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሥርዐት የወንጀል ፍርድ ሂደት የተጠርጣሪን እና የተከሳሽን እንዲሁም የወንጀል ተጎጅዎችን ሰብዓዊ መብቶችን ለማክበርና ለማስከበር፣ የሕግ የበላይነትን ለማስፈን የሚያስችል ወጥ እና የተሟላ ሕግ ማውጣት በማስፈለጉ፣ ሀገሪቱ በወንጀል ፍትሕ ሥርዐት በዓለም አቀፍ ሕግ ያሏትን መብቶች ለማስከበርና የተጣሉባትን ግዴታዎች ለመወጣት የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ በማስፈለጉ፤
የወንጀል ፍትህ አስተዳደሩ ለጠቅላላው ጥቅም እንዲሰራ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑና የወንጀል ክርክር የሚመራበትን የሥነ-ሥርዐትና የማስረጃ ድንጋጌ ወጥና አካታች በሆነ መልኩ እንደገና ማደራጀት በማስፈለጉ፣ እና በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ (፩) እና ፶፭ (፭) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
ሰነድ፡
Comments