ሕግ-ነክ ሰነዶች/ MIRH/ 20 መስከረም 2015
በ-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ዜጎች በየደረጃው በሚካሄድ ነጻ፣ ፍትሃዊና ሰላማዊ ምርጫ በመረጧቸው ተወካዮች አማካኝነት ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር ሥልጣናቸውን በተግባር እንዲያውሉ ለማድረግ ነጻ የምርጫ አስፈጻሚ አካል አስፈላጊ በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ዲሞክራሲን ለማጠንከር ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ከማንኛውም አካል ነጻ አድርጎ በማደራጀት ፍትሃዊ፣ ተዓማኒና ሰላማዊ ምርጫ ለማስፈጸም የሚያስችለው መዋቅር እንዲኖረው ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላትን አመላመልና አሿሿም አሳታፊና ግልጽ በማድረግና የቦርዱን የመዋቅር፣ የሰራተኛ ቅጥርና ምደባ እንዲሁም የበጀት ነጻነት በማረጋገጥ በተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶችና በመራጩ ዘንድ ያለውን ተዓማኒነትና የማስፈጸም አቅሙን ማሳደግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራያዊ ሪፐብክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ ፶፭(፩) እና (፩፻፪) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
Comments