ሕግ-ነክ

የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ

ሕግ-ነክ ሰነዶች/ MIRH/ 24 መስከረም 2015

በ- የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ

ኢትዮጵያዊያን በማንኛውም ሁኔታ ልዩነት ሳይደረግባቸው በቀጥታ እና በነፃነት በመረጧቸው ተወካዮች አማካኝነት ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር ስልጣናቸውን በተግባር ላይ ማዋል አስፈላጊ በመሆኑ፤

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየደረጃው በሚደረጉ ሁሉን አቀፍ ነፃ፣ ፍትሃዊና ሰላማዊ ምርጫዎች በእኩልነትና በነጻነት በሚስጢር ድምፅ አሰጣጥ ፈቃዱን በመግለጽ የመሳተፍ መብቱን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤

ማንኛውም የምርጫ እንቅስቃሴ ዓለም አቀፍ የምርጫ መርሆዎችን አካትቶ በያዘ ህግ እንዲመራ ማድረግ በማስፈለጉ፤

የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያየ ዓላማና አመለካከታቸውን በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ለመራጩ ሕዝብ በመግለጽ የሚሳተፉበት፣ መራጩ ሕዝብም በመረጃ ላይ በመመስረት ፈቃዱን በነፃነት በመግለፅ ወኪሎቹን የሚመርጥበት የምርጫ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤

ዜጎች በሚመሠርቱት ወይም በአባልነት በሚቀላቀሉት የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ የሚኖራቸውን መብትና ግዴታ፥ እንዲሁም ፓርቲው ሕጋዊ ሰውነት የሚያገኝበትን ሁኔታ እና በድርጅትነት ሲንቀሳቀስ መከተልና ማክበር ያለበትን መሠረታዊ መርሆች መደንገግ በማስፈለጉ፤

የፖለቲካ ፓርቲዎች በመዋሀድ፣ ግንባር በመፍጠር ወይም በመቀናጀት ሊንቀሳቀሱ የሚችሉበትን ሁኔታ መደንገግ አስፈላጊ በመሆኑ፤

ለፍትሃዊ፣ ሰላማዊ፣ ነፃና ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ሥርዓት መስፈን በምርጫ የሚሣተፉ የፖለቲካ ድርጅቶችና የግል ዕጩዎች ገንቢ አስተዋጽኦ የሚያደርጉበትን ግልፅ አሰራር መዘርጋት በማስፈለጉ፤

ምርጫዎች በመልካም ሥነ ምግባር የሚመሩ ነጻ፣ ፍትሃዊ ፣ሰላማዊ፣ ሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆኑና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነትን እንዲያገኙ ለማድረግ በምርጫ ወቅት የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎች፣ አባላት እና ደጋፊዎች የሚመሩባቸውን የሥነ ምግባር መርሆች መደንገግ አስፈላጊ በመሆኑ፤

በምርጫ ሂደት ለሚነሱ አለመግባባቶች አስተዳደራዊ እና የዳኝነት መፍትሔ የሚሰጡ ተቋማትን እና አሰራራቸውን መወሰን በማስፈለጉ፤

በገለልተኝነት ምርጫን እንዲያስፈጽም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ ቁጥር ፩ሺ፩፻፴፫/፪ሺ፲፩ መልሶ መቋቋሙን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባቱ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭(፩) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

ሰነድ፡

የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ

የምርጫ ማስፈጸሚያ ቁሳቁሶችና እና ሰነዶች ድልድል፣ ሥርጭት፣ አጠቃቀም፣ ርክክብና አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 8/2013

Previous article

በአዲሱ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ህግ የተለወጡ ዋና ዋና ጉዳዮች

Next article

You may also like

Comments

Leave a reply