የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን

MIRH/ 10 መስከረም 2015

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ከዚህ በኋላ “ባለሥልጣን” እየተባለ የሚጠራ የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግስት መስሪያ ቤት ሆኖ በኢዲስ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ተቋቁማል። የባለስልጣኑ ተጠሪነት ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው።

የባለሥልጣኑልጣንና ተግባራት

የብሮድካስት አገልግሎት የፈቃድ ሁኔታን ይወስናል፣ ፈቃድ ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፤

በብሮድካስት አገልግሎት ለመሰማራት የሚያስችል የብቃትና የቴክኒክ ማረጋገጫ መስፈርት መመሪያ በማዘጋጀት በቦርድ ያስወስናል። በመመሪያው መሰረትም የብቃትና የቴክኒክ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፤

ሥርጭቱ ከአንድ ክልል በላይ የሆነ በጊዜው በሚወጣ የህትመት ሥራን ወይም የዜና አገልግሎት ሥራን ወይም የበይነመረብ መገናኛ ብዙሃንን በመመዝገብና የምዝገባ ምስክር ወረቀት በመስጠት ሕጋዊ እውቅና ይሰጣል፤

በየጊዜው የሚወጣ የህትመት፣ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃንና የዜና አገልግሎት ምዝገባ የብሮድካስት ፈቃድ የፈቃድ ማሳደሻ እና የብቃትና የቴክኒክ ማረጋገጫ አገልግሎቶች ክፍያዎችን መንግስት በሚያጸድቀው ተመን መሠረት ይሰበስባል፤

የመገናኛ ብዙኃን ሥራዎችን በሕግ አግባብ ማከናወናቸውን ለማረጋገጥ በሕገ መንግስቱ በዚህ አዋጅና በዚህ አዋጅ መሠረት በሚወጡ ደንብና መመሪያ እና ሌሎች አግባብነት ባላቸው ሕጎች መሠረት ቁጥጥር ያደርጋል፤

በማስተወቂያ ሕግ መሠረት ማስታወቂያን ይቆጣጠራል፤

የብሮድካስት አገልግሎት እና የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃንን በተመለከተ በዜጎችና ተቋማት የሚቀርቡትን ቅሬታዎች አንዲሁም በባለፈቃዶች መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል፤

ስለመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ዕድገትና መሻሻል ጥናትና ምርምር ያደርጋል፣ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፉን የሚመለከቱ መረጃዎችን አጠናቅሮ ይይዛል፤

የፖሊሲና የሕግ ሀሳቦችን ያመነጫል፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተማክሮ ለመንግስት ውሳኔ ያቀርባል፣ ሲፀድቀም ተግባራዊ ያደርጋል፤

የመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ ባለድርሻ አካላት በመደበኛነት የሚወያዩበትን መድረክ ማመቻቸትን ጨምሮ በመገናኛ ብዙኃንና በመንግስት አካላት መካከል መልካም የሥራ ግንኙነት እንዲኖርና እንዲጠናከር የሚያስችሉ ተግባራትን ያከናውናል፤

የመገናኛ ብዙኃንን አቅም ለማሳደግ የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ ማድረግን ጨምሮ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ያከናውናል በዚሁ ሥራ ላይ ከሚሰማሩ ሲቪል ማህበራት የትምህርት የጥናትና ምርምርና የሥልጠና ተቋማት ጋር በትብብር ይሰራል፣ የመገናኛ ብዙሀንን አቅም ለመገንባት የሚያስችለውን የሥልጠና ማዕከል ያቋቁማል፤

በብሮድካስት አገልግሎት እና የበይነመረብ መገናኛ ብዙኃን የሚሠራጩ ፕሮግራሞች የሚመሩበትን ዝርዝር የሥነ ምግባር መመሪያ ያወጣል፣ የእርስ በእርስ ቁጥጥር ያላቸው የመገናኛ ብዙሃን አደረጃጀቶች አስተያየት እንዲሰጡበት አተገባበሩ ላይም እንዲሳተፉ ያደርጋል፤

የመገናኛ ብዙሃን የእርስ በእርስ ቁጥጥርና ግምገማ አደረጃጀትና አሰራር እንዲጠናከር ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል፤

ለመገናኛ ብዙሃን ዘገባ ሥራ ከውጭ ሀገር ለሚመጡም ሆነ ተቀማጭነታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ለሆኑ የውጭ ሀገር መገናኛ ብዙሀን እና የዜና ወኪሎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው እንዲሰሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፣ አስፈላጊ ሰነዶች መሟላታቸውን በማረጋገጥ ይመዘግባል።

ራዕይ:- አስተማማኝ የመገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ እውን ሆኖ ማየት

ተልዕኮ:- በአስቻይ ቁጥጥር፣ አቅም ግንባታ እና አጋርነት፤ ብዝኃነቱ የተረጋገጠ እና በኃላፊነት የሚሰራ የመገናኛ ብዙኃን ማጎልበት

እሴት:- ገለልተኛ፣ ውጤት ተኮር፣ ትብብር፣ ልህቀት

አድራሻ፡-

ድረገጽ፡- https://www.ema.gov.et    

ስልክ፡- 0115538759

ሰለሞን ተሰማ፡ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ስፖርት ጋዜጠኛ

Previous article

አዲስ ማለዳ – ዜና ከምንጩ

Next article

You may also like

Comments

Leave a reply