አውደ ጥናት/MIRH/ 27 የካቲት 2015(23)
የኢትዮጵያ ናሽናል ሚዲያ ሳፖርት (ENMS) ከIMS-PRIMED ጋር በመተባበር “የኢትዮጵያ ሚዲያ ግጭት አገናዛቢነት እና የሰላም ግንባታ” በሚል የካቲት 14፣ 2015 ዓ.ም በአዘማን ሆቴል ሲካሄድ የቆየው የባለድርሻ አካላት ውይይት ባለ13 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡
በእለቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በአቶ ፍቃዱ ዓለሙ፣ የENMS ዋና ዳይሬክተር የቀረበ ሲሆን የእለቱን የመወያያ አጀንዳ አስመልክቶ ለተሳታፊዎች ዋና መልክት ያስተላለፉት ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ ዋና ዕንባ ጠባቂ፣ ክቡር ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ናቸው፡፡ የመገናኛ ብዙሃን ባለቤቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ከፍተኛ የመንሥት ባለሥልጣናት፣ የወጣት ፌዴሬሽን አባላት፣ ማኅበራት፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና የሚዲያ ልማት ድርጅቶች በጉባኤው ተሳትፈዋል፡፡
ስለግጭት አገናዛቢነት እና ሰላም ግንባታ የውይይት መነሻ ጽሑፍ በዶ/ር ተሻገር ሽፈራው (ፒ.ኤች.ዲ)፣ ረዳት ፕሮፌሰር፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ሥነ ተግባቦት መምህር የቀረበ ሲሆን ሌሎች ሦስት የሚዲያ ባለሙያዎች ከግጭት አገናዛቢነት ጋር የተገናኙ ልዩ ልዩ ሙያዊ ምልከታዎችን ለተሳፊዎች አቅርበዋል፡፡
ከሰዓት በኋላ በጥያቄና መልስ የቀጠለው ውይይት ኹሉም ባለድርሻ አካላት የደረሱበትን ጭብጥ አስመልክቶ ባለ13 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
እባክዎን ከታች የተያያዙትን ማጣቀሻዎች/ሊንኮች ያስፈንጥሩና የአቋም መግለጫዎቸን ያንብቡ
https://drive.google.com/file/d/1i3hIHKFRE3AZtr70DwlDtM9EwTtLkt9r/view?usp=sharing
https://drive.google.com/file/d/1erWYj2cF_wGE26t7rZG_l98B6G1_FaPv/view?usp=sharing
Comments