የኢትዮጵያ ሚደያ ፕሮፋይል

መረጃ ለማህበረሰብ ግንባታ ቁልፍ መሳሪያ ነው፡፡ የመረጃ ቅብብሎሽ የሚጀመረው ደግሞ ከሰው ልጅ መፈጠር ጀምሮ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ጽህፈት ባልዳበረበት በጥንት ጊዜ ሰዎች ነጋሪት፣ መለከት፣ ጥሩንባና ሌሎች ባህላዊ መሳሪያዎችን ተጠቅመው በስዕል፣ በዘፈን፣ በግጥም እና በስነ ቃል መረጃዎችን ይለዋወጡ ነበር፡፡ አዝማሪዎችና እረኞች ጋዜጠኛ ሆነው ያገለግሉ እንደነበር የኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ታሪክ ያሳያል፡፡

ዛሬ ላይ ከቴክሎጂ መዘመን ጋር ተያይዞ የመረጃ መለዋወጫ ዘዴዎች እየሰፉ መጥተዋል፡፡ ጋዜጣ፣ መፅሄት፣ ብሮሸር፣ ፓምፕሌት፣ ሊፍትሌት፣ ሬዲዩ፣ ቴሌቪዥን እና ኢንተርኔት ሁነኛ የመረጃ ምንጮች ሆነዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከባለቤትነት አኳያ በርካታ የሕዝብ፣ የግል እና የማህበረሰብ ተኮር መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ተቋቁመዋል፡፡ አሁን በስራ ላይ የሚገኙት ብሎም የሌሉትን ታሪክ በማስፈንጠሪያዎቹ አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ፡፡

በዘመን አመጣሹ ኢንተርኔት አማካኝነት እየተበራከቱ የሚገኙ የበይነመረብ መገናኛ ብዙሃን እና የጋዜጠኝነት ትምህርት የሚሰጡ ተቋማት ታሪክም ይዳሰሳል፡፡ በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ አሻራቸውን ጥለው ያለፉ ባለሙያዎች የህይወት ታሪክ ሌላኛው ግብአት ነው፡፡ ማስፈንጠሪያዎቹን ተጠቅመው ያንብቧቸው፡፡