ደንብ/ MIRH/ 30 የካቲት 2015
በኢትዮጵያ ሚዲያ ካውንስል (EMC)
ይህ ደምብ በኅዳር ወር 2015 ዓም የታተመ ሲሆን የሚዲያ ባለሞያዎች የጋዜጠኝነት የሙያ ሥነ ምግባርን ጠብቀው እና ሙያው በሚያዘው መሰረት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማገዝ ታስቦ የተዘጋጀ ደምብ ነው፡፡ ደምቡ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ዘገባዎችንም ሆነ ፕሮግራሞችን በሚያዘጋጁበት ወቅት በምን መልኩ ማዘጋጀት እና ለተደራሲው እንዴት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል የሚለውን በስፋት የሚያብራራ እና ባለሞያዎችን የሚያግዝ ደንብ ነው፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት አባል የሆኑትን መገናኛ ብዙሃ እና የበይነ መረብ ሚዲያ ተቋማትና በእነዚህ ተቋማት የሚሠሩ ባለሞያዎችን ተግባራት ለመምራት ታቅዶ የተዘጋጀ ነው፡፡ ይህ ደምብ ይገዛኛል ብለው የሚያምኑ ባለሞያዎችም በዚህ እትም የተካተቱን ዝርዝር መመሪያዎች እና ደምቦችን ማክበር ይጠበቅባቸዋል፡፡
ዝርዝር ደንቡን ለማግኘት ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑት
https://drive.google.com/file/d/1Ul6BiZ4AyTQGpmzxJlGOz2KPoSy7VpPB/view?usp=sharing
Comments