መመሪያዎች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳር ቢሮ የመንግስት ቤቶች አስተዳደር መመሪያ

መመሪያዎች/ MIRH/ 12 ሐምሌ 2014

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንብረት የሆኑትን የመንግስት የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ትክክለኛ መረጃዎችን በማደራጀት በተገቢው በማስተዳደር ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል፣ ወጣቶችን፣ ሴቶችንና ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የአካል ጉዳተኞችን ከቤት አስተዳደር ሥርዓቱ ይበልጥ ተጠቃሚነቱን የሚያረጋግጥ አሰራር መፍጠር በማስፈለጉ፤

የከተማው አስተዳደር ቤቶች እድሳት ሳያገኙ በመቆየታቸውና በከተማ ማደስ ፕሮግራም አማካይነት እየፈረሱ ያለበት ሁኔታ በአግባቡ በመለየትና መረጃቸውን በመያዝ ቀጣይ የቤት ግንባታ ዕቅዶችና አቅጣጫዎችን ለመቀየስ የሚያስችል አቅም እንዲኖር ማድረግ በማስፈለጉ፤

የከተማው አስተዳደር ቤቶች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አያያዝና አጠባበቅ ሁኔታ ለክትትልና ቁጥጥር አመቺ እንዲሆን በማድረግ በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የመንግስት ቤቶችን ያለአግባብ መጠቀምና ወደ ግል ይዞታ የማዞር ሕገ ወጥ ተግባራትን በመግታት የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ በማስፈለጉ፤

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈጻሚ አካላትን እንደገና ለማደራጀት፣ ስልጣንና ተግባራቸውን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ (3) (ሠ) በተሠጠው መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

 

መመሪያውን ለማንበብ፡

የመንግስት_ቤቶች_አስተዳደር_መመሪያ_2013_2

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ

Previous article

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች፡ ቅፅ 5

Next article

You may also like

Comments

Leave a reply