ሕግ-ነክ

የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ

ሕግ-ነክ ሰነዶች/ MIRH/ 13 ሐምሌ 2014

ተቋማት ሲደራጁ የተሰጣቸውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት በሚያስችል መልኩ ግልጽ ዓላማ ያላቸው፣ ከሌሎች ተቋማት ሥልጣንና ተግባር ጋር የማይጋጭና ተናባቢ የሆነ ተግባርና ኃላፊነት እንዲኖራቸው በማድረግ፣ በቅንጅት የሚሰሩ፣ ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ የሆነ፣ ብክነትን የሚቀንስና ውጤታማነትን የሚያበረታታ፣ ኃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የአስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

የአስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት፣ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በየጊዜው የሚወጡ ሕጎች ወጥ የሆነ የተቋማት አደረጃጀትና ስያሜ ለመፍጠር ያልቻሉ በመሆኑ የተቋማት ቀጣይነትን ለማረጋገጥና የስያሜ ወጥነትን ለማስቀጠል ያልተቻለ በመሆኑ፣

በሥራ ላይ ያለውን የተቋማትን አደረጃጀትና ስያሜ ችግሮች በዝርዝር በጥናት በመለየት በየጊዜው የማይለዋወጥ፣ ዘላቂነት ያለው እንዲሁም ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ጋር አብረው እየተለወጡ የሚሄዱ የተቋማት አደረጃጀትና ስያሜን መፍጠር የሚያስችል ሥርዓት በሕግ መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፣

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌደራል መንግሥት ሕገ-መንግሥታዊ ሥልጣንና ኃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችለው አወቀቃቀር መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፣ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ ፶፭(፩) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።

 

ሰነድ፡

የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ

ፀጋዬ ታደሰ- በኢትዮዽያ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የውጪ ብዙሃን መገናኛ ዘጋቢ

Previous article

የፌደራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ  

Next article

You may also like

Comments

Leave a reply