ሕግ-ነክ

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ

ሕግ-ነክ ሰነዶች/ MIRH/ 11 ሐምሌ 2014

አሠሪና ሠራተኛ የጋራ ራዕይ ኖሯቸው የሥራ ግንኙነቶቻቸውን መሠረታዊ በሆኑና በህግ በተደነገጉ መብቶችና ግዴታዎች ላይ በመመስረት አስተማማኝ የኢንዱስትሪ ሰላም፤ የዘላቂ ምርታማነት እና የገበያ ተወዳዳሪነት አቅም በመፍጠር ሀገራችን ለተያያዘችው ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት የማስመዝገብ ብሔራዊ ግብ በትብብርና በጋራ እንዲሰሩ ማድረግ ጠቃሚ በመሆኑ፤

ሠራተኞች እና አሠሪዎች የየራሳቸውን ማኅበራት በሙሉ ፈቃድና ነፃነት በማቋቋም በመረጧቸው ህጋዊ ወኪሎች አማካኝነት መብትና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅና ግዴታዎቻቸውን በአግባቡ ለመወጣት የኅብረት ድርድር እንዲያደርጉ፤ በመካከላቸው የሚነሱ የሥራ ክርክሮችም የማኅበራዊ ምክክር ሥርዓትን ጨምሮ በሌሎች አማራጭ መድረኮች በተቀላጠፈ ሁኔታ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤

መሠረታዊ የሥራ ላይ መብቶችንና ግዴታዎችን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለኢንቨስትመንትና ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ግቦች መሳካት ምቹ ሁኔታን መፍጠር የሚያስችል የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አስተዳደር ሥርዓት መመስረት እንዲቻል፤ እንዲሁም የሥራ ሁኔታን፤ የሙያ ደህንነት፤ ጤንነትና የሥራ አካባቢ ጥበቃንና የሁለትዮሽ እና የሦስትዮሽ ማኅበራዊ ምክክር አሠራርን በማጠናከር በሕግ መሠረት የማማከርና የመቆጣጠር ተግባራትን እያመጣጠነ ሥራውን የሚያከናውን አካል ስልጣንና ተግባር መዘርዘርና መወሰን በማስፈለጉ፤

እነዚህን ከላይ የተመለከቱትን ዓላማዎች በትክክል መተግበር ይቻል ዘንድ የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነቶች የሚመሩባቸውን መሠረታዊ ሃሣቦች እና የሥራ ሁኔታዎችን የያዘ፤ ከመንግሥት አጠቃላይ የፖለቲካ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ፖሊሲ ጋር የተገናዘበ፤ ኢትዮጵያ ከፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽኖችና ሌሎች ሕጋዊ ሠነዶች ጋር የተጣጣመ ሕግ ለማውጣት በሥራ ላይ ያለውን የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ በአዲስ መተካት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ ፶፭ (፩) እና (፫) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡-

 

ሰነድ፡

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ

 

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ውሣኔዎች: ቅፅ 19

Previous article

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳር ቢሮ የመንግስት ቤቶች አስተዳደር መመሪያ

Next article

You may also like

Comments

Leave a reply