መመሪያዎች

የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረገው ውይይት የሚመራበት ሥርዓት እና ደንብ

መመሪያዎች/ MIRH/ 24 መስከረም 2015

በ-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

በመላ አገራችን ሰላም እና መረጋጋት የሚፈጠርበትን ሁኔታ በጋራ ጥረት እና ተሳትፎ ለማረጋገጥ ሁሉንም ፓርቲዎች ያሳተፈ ውይይት ማድረግ ተገቢ በመሆኑ፤

አገራዊ ምርጫ ነፃ ፍትሐዊና ተአማኒ እንዲሆን የሚያስችሉ የፖለቲካና የሕግ ለውጦች መከናወናቸውን ለማረጋገጥ፤ የዲሞክራሲ ተቋማትን በጋራ ለመገንባት እንዲቻል በፓርቲዎች መሃል ሊኖር የሚገባውን ትብብር ለማሳደግ፤

በፖለቲካ ፓርቲዎች መሀከል አስፈላጊ ከሆነው ፉክክር ውጭ የሚታየውን ያለመተማመን በማስወገድ የጋራ ራዕይን ለመገንባት፤

በአገሪቱ እየተካሄደ ባለው ለውጥ (Reform) ምክንያት የተከሰቱ ችግሮች ላይ ተወያይቶ በጋራ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ሃሳቦችን በጋራ ለማዳበር በፓርቲዎች መካከል ውይይት ማካሄድ ጠቃሚ መሆኑ ስለታመነ፤

እስከአሁን በአገሪቱ ያለው የፖለቲካ ባሕል የሚሻሻልበት ሁኔታ ለማመቻቸት፤ በፓርቲዎች መካከል በጨዋነት እና በመከባበር ላይ የተመሠረቱ ውይይቶች በማድረግ ድርጅታዊ ትብብርን በመፍጠር የዲሞክራሲ አድማሱን ማስፋት አስፈላጊ በመሆኑ፤

የፌዴራል የሕዝብ ተወካዮች የክልል ምክር ቤቶች ውክልና በአንድ ፓርቲ የተያዘ በመሆኑ እና ሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሃሳባቸውን የሚገልፁበት መድረክ ስለሌለ በፖለቲካ ፓርቲዎቹ መሀከል ሊኖር የሚገባውን ውይይት በቀጣይነት የሚያስተናግድ መድረክ አስፈላጊነቱ ተቀባይነት ስላገኘ፤

ይህን የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት የሚመራበትን ደንብ ማውጣት አስፈልጓል፡፡ ስለሆነም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በዚህ የውይይት ስርዓት እና ደንብ ለመገዛት ስምምነት አድርገዋል፡፡

ሰነድ፡

የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረገው ውይይት የሚመራበት ሥርዓት እና ደንብ

በአዲሱ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ህግ የተለወጡ ዋና ዋና ጉዳዮች

Previous article

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

Next article

You may also like

Comments

Leave a reply