ማህበረሰብ ተኮር መገናኛ ብዙሀን ፕሮፋይል

የሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ ማኅበረሰብ ሬድዮ

የሲቪል ሰርቪስ ማህበረሰብ ሬድዮ/ MIRH/ 08 ግንቦት 2015

በመቅደስ ማንአለ

የሲቪል ሰርቪስ ኤፍ ኤም 100.5 ማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ ለኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ ማህበረሰብ እና አካባቢው አገልግሎት ለመስጠት በማሰብ በ2003 ዓ.ም ሕጋዊ ፈቃድ በመውሰድ ሚያዚያ 2008 ዓ.ም የሙከራ ሥርጭቱን በማብሰር ሥረውን አሐዱ ብሎ ጀመረ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ሬዲዮ ጣቢያው ለዩንቨርስቲው ማህበረሰብ እና ለአካባቢው በቀን የአምስት/5/ ሰዓታት ሥርጭት ይሰጣል፡፡

ሬዲዮ ጣቢያው በብሮድካስት አዋጅ ቁጥር 533/07 አንቀፅ 16 የሬዲዮ ስርጭት ፈቃድ የወጣ ሲሆን በቁጥር 33/2003 የማህበረሰብ ሬድዮ ባለቤትነት አና በተመደበለት ፍሪኮንሲ 100.5 የተመዘገበ ነው፡፡ የሲቪል ሰርቪስ ኤፍ ኤም 100.5 ማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ በሥርዓተ ፆታ፤ በወጣቶች፤በአካባቢ ጥበቃ፤ ጤና ነክ ጉዳዮች የሚዳሰሱበት እና የዩኒቨርሲተውን ማህብረሰብ የሚያስተምሩ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተው ይቀርቡበታል፡፡ ይህ የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ በየጊዜው የማህበረሰቡን ገንቢ ተሳትፎና አስተያየቶች በማጠናከር ለለውጥ የሚተጋ የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ እንደሆነ የጣቢያው የማኔጅመት ሠራተኞች ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚጠቅሙ ርእሰ ጉዳዮች የተደረጉ የጥናትና ምርምር ውጤቶችን ጨምሮ በመደበኛ ፕሮግራሞችን ያሰራጫል፡፡

ሬዲዮ ጣቢያው በአሁኑ ሰዓት 11 መደበኛ ባለሙያዎች እና 6 በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎች ያሉት ሲሆን ከሥርጭት አንጻር ወደ ፊት በአዲስ አበባ እና ዙሪያ ተደማጭ ለመሆን ከአምስት ሰዓት ወደ ዐስር ሰዓት ለማሳደግ አቅዶ እየሠራ ይገኛል፡፡

የዲላ ዩንቨርሲቲ ማኅበረሰብ ሬድዮ ኤፍ ኤም

Previous article

ዶይቸ ቬለ (DW) የጀርመን ዓለም አቀፍ ብሮድካስት

Next article

You may also like

Comments

Comments are closed.