ማዕረጉ በዛብህ: ጋዜጠኛ፣ መምህርና ዲፕሎማት

የሚዲያ ባለሞያዎች መዝገብ / MIRH/ 28 ጥቅምት 2015 በአቢ ፍቃዱ ማዕረጉ በዛብህ ከአባቱ ከፊታውራሪ በዛብህ ይማምና ከእናቱ ከወይዘሮ ይምባወርቅ ሺበሺ በ1930 በወሎ ክፍለ ሀገር፣ በዋግ አውራጃ ኮረም ከተማ ተወለደ፡፡ ማዕረጉ ገና ሦስት ዓመት ሳይሞላው ፊታውራሪ በዛብህ ከፋሽስት ኢጣሊያ ጋር በአርበኝነት ሲዋጉ ተሰውተዋል፡፡ ማዕረጉ ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን የተማረው በመቀሌና በአዲስ አበባ ነበር፤ በአጼ ዮሐንስ አራተኛ፣ በኮከበ ጽባህና በአስፋወሰን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በጄኔራል ዊንጌት ...