ሕግ-ነክ

የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ

ሕግ-ነክ/ MIRH/ 3 ታህሳስ 2021

መገናኛ ብዙሃን ለሕዝብ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በማቅረብ፣ በማሳወቅ፣ በማስተማርና በማዝናናት እንዲሁም የዜጎችን ሀሳብን የመግለጽ ሕገ መንግስታዊ መብት ተግባራዊ በማድረግ እና የተለያዩ አመለካከቶችንና አስተያየቶችን በማስተናገድ ለዲሞክራሲ ስርዓት መዳበር ተፈላጊ የሆነው ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠርና እንዲጎለብት የሚያደርግ መሳሪያ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት ሀሳብን በነፃ የመያዝና የመግለጽ ነፃነት የተረጋገጠ ከመሆኑ በተጨማሪ ፕሬስ በተቋምነቱ የአሰራር ነፃነት ኖሮት የተለያዩ አስተያየቶችን የማስተናገድ ችሎታ እንዲኖረው የሕግ ጥበቃ ተደርጎለታል፡፡ ይሁንና በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ የሚመራበት ራሱን የቻለ የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ ባለመኖሩ ዘርፉን በብቃት እና በጥራት በማስፋፋት ሁሉንም የኢትዮጵያ ዜጎች የመረጃ ተደራሽ ማድረግ አልተቻለም፡፡

ይህን የመገናኛ ብዙሃን ፖሊሲ በማዘጋጀት ሂደትም የዘርፉን ዋና ዋና ችግሮች እና
መከናወን የሚያስፈልጋቸውን ወሳኝ ጉዳዮች ለይቶ ለማወቅ በሀገር አቀፍ ደረጃ ጥናት ተደርጓል፣ ነባራዊ ሁኔታውም ተገምግሟል፡፡ በጥናቱ ግኝት መሰረትም የመገናኛ ብዙሃን የሚመሩበት ምቹ የሕግ ማእቀፍ አለመኖሩ፣ የመረጃ እጦት ወይም እጥረት ያለባቸው መሆኑ፣ መገናኛ ብዙሃን ሁሉን አቀፍ ተደራሽነት የሌላቸውና ብዝሃነትን እና ጥራትን ጠብቀው የተስፋፉ አለመሆናቸው፣ በስራ ላይ ያሉት ሕጎች የጋዜጠኞችን የስራ ነጻነት የሚጋፉ መሆናቸው የሚሉት ከተለዩ ዋና ዋና ችግሮች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

 

በENMS በተዘጋጀው የምክክር ስብሰባ ላይ የቀረበ የጥናት ወረቀት

Next article

You may also like

Comments

Comments are closed.