ኢትዮጵያ

የመገናኛ ብዙሃን የርስ በርስ ቁጥጥርን ተግባራዊ ማድረጊያ መንገድ በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ/MIRH/ 17 ጥር 2022

በፍቃድ አለሙ

መግቢያ

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን የቁጥጥር ስርዓት ምን መምሰል አለበት በሚለው ሃሳብ ላይ የሚነሳው ክርክር በሕግ ምላሽ ያገኘው በአዲሱ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2021 ነው፡፡ በአስገዳጅ ሕግ ላይ ያልተመሰረተ የመገናኛ ብዙሃን የጋራ ቁጥጥር ስርዓት መዘርጋቱ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ራሱን በራሱ እንዲቆጣጠር እድል ሰጥቶታል፡፡ የተጋጋለ ብሔርተኝነት፣ የማህበረሰብ ግጭት እና የዜጎች መፈናቀል የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ሽግግር በተደጋጋሚ እየፈተነ ያለ ጉዳይ ቢሆንም ሃገሪቱ ለበርካታ የማህበረሰብ አደረጃጀቶች ፈቃጅና አካታች የሆነ ምህዳር በመፍጠር ላለፉት ሦስት ዓመታት በዲሞክራሲ ሸግግር ውስጥ በማለፍ ላይ ትገኛለች፡፡ በሂደት ላይ ያለውን አካታች የለውጥ ፕሮግራም እና የፖሊሲ ስነ ምህዳር መስፋት ተከትሎ የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ተዋንያን በሀገሪቱ የርስ በርስ ቁጥጥር ስርዓት ውስጥ ያላቸውን ሚና በማሳደግ እንዲሁም የርስ በርስ የቁጥጥር አካሉ በአገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን የአስተዳደር ስርአት ውስጥ ያለውን የቁጥጥር ሚና ለማሳወቅ የሚረዱ የህግና የአስተዳደር እርምጃዎችን ለመውሰድ የጋራ ትብብር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ለሶስት አስርት ዓመታት ያህል በአምባ ገነን የመንግስት ስርዓት ውስጥ ሆን ተብሎ ሲዳከም በቆየው የመገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ውስጥ እንዴት ጠንካራና ውጤታማ የርስ በርስ ቁጥጥር ስርዓት መገንባት ይቻላል የሚለው ጥያቄ አሁንም መሰረታዊ ተግዳሮት ነው፡፡ በአሁን ጊዜም ቢሆን ቀደም ሲል የነበረውን የተቋም ባህል በማስቀጠል ረገድ በአዲስ መልክ ጥብቅ የቁጥጥር ስርዓትን የመዘርጋት ሁኔታ ይስተዋላል፡፡ እየቀጠለ የመጣው የዘርፉ በፖለቲካ ባለቤትነት ተፅእኖ ስር የመውደቅ ሁኔታ የዘርፉን ታአማኒነት በመሸርሸር፤ የህዝብ አመኔታን ለማግኘት የሚጓዝበትን መንገድ ይበልጥ ውስብስብ እያደረገው ይገኛል፡፡

MIRH content review and validation workshop

Previous article

የመገናኛ ብዙሃን ማሻሻያ ላይ የተነሱ ሃሳቦች

Next article

You may also like

Comments

Leave a reply