ኢትዮጵያ

የመገናኛ ብዙሃን ማሻሻያ ላይ የተነሱ ሃሳቦች

ኢትዮጵያ / MIRH/ 17 ጥር 2022

በፍቃድ አለሙ

የዚህ መጽሔት ይዘት እና የጸሐፊዎቹ ስብስብ ቅንጅት የተጀመረው እ.ኤ.አ በየካቲት 2019 መጀመሪያ አካባቢ በአንድ ሆቴል የቦርድ ክፍል ውስጥ በብዙ የኢትዮጵያ ቡና ብርታት ሰጪነት በነበረ ስብሰባ ነበር፡፡ ይህ መጽሔት ይህን ቅርፅ እንዲይዝ የተሳተፉት የኑቢያ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ሀድራ አህመድ ፣ ምክትል ስራ አስኪያጅ ንጉሱ ሶሎሞን ፣ የስነ-ፆታ ባለሞያዋ ሰላም ሙሴ ፣ ማሪካ ግሪሼል እና እኔ ነበርን፡፡ ስለዚህ የዚህ መጽሔት ጅማሮ የሶስት ሀገር ዜጎች የኢትዮጵያ ፣ ስዊድን እና ደቡብ አፍሪካ ጋዜጠኞች የቡድን ጥረት ነበር፡ ፡

በዚህ መጽሔት ላይ በመፃፍ የተሳተፉት አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ቢሆኑም እንደ ዚምባብዌ ፣ ኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ ካሉ ሃገራት የመጡ ጋዜጠኞች እና ባለሞያዎች እንዲሁም ከአህጉራችን ውጪ የተሳተፉ ጥቂት ፀሐፍያን ሲኖሩ መጽሔቱ ዓለም አፍሪካዊ መነሻ ኖሮት አለም አቀፋዊ ተቀባይነት እንዲኖረው ያደርጉታል፡፡ ይህ መጽሔት ዕውን እንዲሆን የረዱ የተወሰኑ ድርጅቶችን እና ግለሰቦችን ማመስገን እሻለሁ፡፡

ላርስ ታለርት ፣ ማሪካ ግሪሼል እና ታታሪውን የፎዮ ቡድን ፣ ለትርፍ ባልቆመው ሊናስ ዩኒቨርሲቲ የሚደገፈውን የስዊድን መገናኛ ብዙሃን እድገት ኢንስቲትዩት ማመስገን እሻለሁ፡፡ አኔት እና የአዲስ አበባ ስዊድን ኤምባሲ ሰራተኞችን ፤ የ ኑቢያ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽኖቹ ሀድራ አህመድ ፣ ንጉሱ ሶሎሞን እና ሰላም ሙሴ ፤ መፅሔቱ ውስት ያሉትን ፎቶዎች ያነሳልን ሚኪ ተወልደ ፤ መጽሔቱን በሚያምር ዲዛይኑ ያስዋበልን ኢዛት አማኑኤል ፤ እንግሊዝኛ ፅሁፎችን ወደ አማርኛ የተረጎመልን ቢንያም ጌታነህ ፤ በመጨረሻም ለዚህ መጽሔት ስኬት ጠንክረው ሲሰሩ የነበሩ ጋዜጠኞችን እና ፀሐፊዎችን አመሰግናለሁ፡፡

የመገናኛ ብዙሃን የርስ በርስ ቁጥጥርን ተግባራዊ ማድረጊያ መንገድ በኢትዮጵያ

Previous article

ተፈላጊ ጋዜጠኞች እንዴት ያሉ ናቸዉ? ቀጣሪዎች ምን ይፈልጋሉ?

Next article

You may also like

Comments

Leave a reply