የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን ፕሮፋይል / MIRH/14 መጋቢት 2014
በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚገኙ የመንግሥት ብሮድካስት አገልግሎት ሰጪ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ዝርዝር ነጻ በሆነ የመረጃ ቋት ውስጥ ማግኘት ጥቅሙ ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ አንድም በሀገር ውስጥ ያሉ የመንግሥት ብሮድካስተሮች እነማን እንደሆኑ ለማወቅ እድል ይሰጣል፡፡ ሁለተኛ እንዲህ ዓይነት መረጃዎች ለኹሉም ግልጽ ሆነው ሲቀርቡ በዘርፉ ያሉ አጥኝዎች እና ተመራማሪዎችን ሥራ በእጅጉ ያቀልላቸዋል፡፡
በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን (Ethiopian Media Authority-EMA) በቅርብ ዓመታት ተሻሽሎ የቀረበው የመንግሥት ብሮድካስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዝርዝር መረጃ ወሳኝ ነው፡፡ መረጃው የመንግስት ብሮድካስተሮችን ብዛት፣ ዓይነት፣ ባለቤትነት እና ሌሎች አስፈላጊ አድራሻዎችን አካቶ ይዟል፡፡ መረጃዎቹ በአጠቃላይ የመንግሥት ሬዲዮና ቴሌቭዥን ብሮድካስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ስም ዝርዝር እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች እንደሚከተለው አሰባስቦ ይዟል፡፡
Comments