ነጋሪት ጋዜጣ (Negarit Gazeta)
ነጋሪት ጋዜጣ ፕሮፋይል / MIRH/ 02 ሚያዚያ 2015 በሳሙኤል አሰፋ መገናኛ ብዙሃን ከዘመን ጋር ዘምነው በተለያዩ እድገት ደረጃዎች አልፈው የ21ኛው ክ/ዘ አሰራር ላይ ከመድረሳቸው አስቀድሞ ዘመኑን በሚመጥን ሁኔታ ሰዎች ሃሳባቸውን የሚለዋወጡባቸው የተለያዩ የግንኙነት መሳሪያዎች ነበሩ፡፡ ከእነዚህ የግንኙነት ሳሪያዎች አንዱ ነጋሪት ነው፡፡ ነጋሪት ከመገናኛ አውታር (Communication Medium) ከመሆን በተጨማሪ ለሙዚቃ መሳሪያነትም ያለገለ ቢሆንም፤ የመገናኛ ብዙሃን አማራጮች ባልተስፋፉበት ዘመን ግን ነጋሪት እንደዋና የመገናኛ ዘዴ ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ ስሪቱ በአብዛኛው ከእንጨት ቢሆንም አልፎ አልፎ ...