መመሪያዎች/ MIRH/ 04 ጳጉሜ 2014
በ-የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስሥልጣን
በሳተላይት ወይም በኬብል አማካኝነት የሚሰራጭ የሃይማኖት ብሮድካስት አገልግሎት የሃይማኖት ተቋማት አስተምህሮታቸውን በብሮድካስት ጣቢያዎች ለማድረስ እንዲሁም በማህበራዊ ጉዳዮች፣ በሠላም ግንባታ፣ በሥነ-ምግባር ዕሴቶች፣ በታሪክ እና መሰል ሃይማኖታዊ እሴቶች ዙሪያ ማሕበረሰቡን ለማስተማር፤ ህብረተሰቡም ባለበት ቦታ ሆኖ ሃይማኖታዊ ፕሮግራሞችን ለመከታተል እንዲችል፤ የሃይማኖት ብሮድካስት ጣቢያዎችም ሃይማኖታዊ ሚናቸውን በተገቢው መንገድ እንዲጫወቱ ለማስቻል፤
የሃይማኖት ብሮድካስት አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ ሂደትን ግልጽ እና ፍትሃዊ እንዲሆን ማድረግ በማስፈለጉ፤
በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 6(1)፣(5) እና 40(3)(ለ)፤ መሰረት የሀይማኖት ብሮድካስት አገልግሎት የፍቃድ አመልካቾች ፍቃድ ለመስጠት እንዲሁም ባለፈቃዶች ሕገ መንግስቱን፣ የአገሪቱን ሕጎች እንዲሁም፤ የሕዝብን ሰላም፣ ደኅንነት፣ የዜጎችን ተነፃፃሪ መብቶችና ጥቅሞች ባከበረ መልኩ በኃላፊነት ስሜት ሥራቸውን ማከናወናቸውን ማረጋገጥ በማስፈለጉ፤
በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 12(7) እና አንቀፅ 90(2) መሰረት ይህ መመሪያ በባለሥልጣኑ ቦርድ ወጥቷል፡፡
ሰነድ፡-
Religious Radio and TV Licensing Directive_899
Comments