የግል መገናኛ ብዙሃን ፕሮፋይል / MIRH/ 30 መስከረም 2015

በመቅደስ ደምስ

ዋን ላቭ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ ኃ/የተ/የግ/ማ የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬዲዮ ጣቢያ ባለቤት ሲሆን ማህበሩ የሶስት ግለሰቦች ንብረት ነው፡፡ ጳጉሜ 1 ቀን 2009 ዓ.ም. የተመሰረተው ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 በሰዎች ወይም ተቋማት መካከል የሚኖር የመረጃ፣ የሀሳብና የአገልግሎት ቅብብሎሽ በዕውቀት፣ በፍትሃዊነት፣ በመተሳሰብና መከባበር ላይ እንዲመሰረት ማድረግ አላማው ነው፡፡

የ18 ሠዓታት ስርጭት ያለው ሬዲዮ ጣቢያው አዲስ አበባን ጨምሮ ስርጭቱ እስከ ምዕራብ ሀረርጌ፣ ሻሸመኔ፣ አሰላ፣ አዳማ፣ ፍቼ፣ መተሃራ፣ ዝዋይ፣ ደብረብርሃንና ስልጤ ዞን በጠቅላላው 300 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ተደራሽ ነው፡፡

45 ሰራተኞች ያሉት ሬዲዮ ጣቢያው ስፖርትን ጨምሮ በሬዲዮ ጣቢያው እና በተባባሪ አዘጋጆች ተዘጋጅተው የሚቀርቡ ከሠላሳ በላይ መረጃ ሰጪና አዝናኝ ፕሮግራሞችን በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ ከእዚህ ባሻገር ዋዜማ ሬዲዮ ከጣቢያው በሳምንት የሁለት ሰአታት የአየር ሰአት ወስዳ ዝግጅቶቿን እያደረሰች ነው፡፡

ዜና፣ ታዲያስ አዲስ፣ የቸገረ ነገር፣ ማራኪ ጤና፣ አስታራቂ እና ኢትዮ አውቶሞቲቭ ከሬዲዮ ጣቢያው ዝግጅቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም ከ107.8 የአየር ሞገድ በተጨማሪ ዲጂታል ቴክኖሎጂው የፈጠረውን ዕድል በመጠቀም ራሱን የቻለ የዲጂታል ሬዲዮ የስራ ክፍል በመፍጠር በስልክ መተግበሪያ፣ በፌስቡክ፣ በድረገጽ፣ በቴሌግራም፣ በዩቲዩብና በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት በመላው አለም ተደራሽ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡

 

አድራሻ፡-

http://www.ethiofm107.com

ኢሜል፡- info@ethiofm107.com

ስልክ ቁጥር፡ +251116686250 /+251116686041

የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረገው ውይይት የሚመራበት ሥርዓት እና ደንብ

Previous article

“የመገናኛ ብዙሃን የሰላም አዘጋገብ በኢትዮጵያ” የኢ ቢ ኤስ (EBS) ቴሌቭዥን “What’s New” ዘገባ

Next article

You may also like

Comments

Leave a reply