የግል መገናኛ ብዙሃን ፕሮፋይል

ኢትዮጵያ ውስጥ የተዘጉ የኅትመት መገናኛ ብዙኃን

የተዘጉ የኅትመት መገናኛ ብዙሃን /MIRH/ 11 ሐምሌ2015

በፍቃዱ ዓለሙ እና በመቅደስ ምንአለ

መግቢያ

በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ አሻራ ካላቸው የሚዲያ ዘርፍ መካከል የኅትመት መገናኛ ብዙሃን ኹነኛ አስተዋጽዖ እንደነበራቸው መረጃዎች ይገልጻሉ፡፡ ይሁንና በአሁኑ ወቀት ዉጥራቸው እየመነመነ የመጣው የኅትመት መገናኛ ብዙሃን ከጥቂት ጋዜጦች (የመንግሥት) በስተቀር በልዩ ልዩ ምክንያት ብዙዎቹ የኅትመት ሚዲያዎች አንድም በወረቀት ኅትመት መወደድ አልያም የዲጅታል ሚዲያ ተጽእኖ መቋቋም ባለመቻላቸው እና በሌሎች ምክንያቶች ከገቢያ እንዲወጡ አስገድዷቸዋል፡፡ በዚህ እትም ከገቢያ የጠፉ ወይም ሙሉ ለሙሉ የኅትመት ሥርጭታቸውን ካቋረጡት መካከል የተወሰኑትን እናስነብባችሃለን፡፡

መሰናዘሪያ ጋዜጣ

መሰናዘሪያ ጋዜጣ ኅትመት ጊዜ የካቲት 2001 ዓ.ም ሲሆን ጋዜጣው ትኩረት አድርጎ ይሠራ የነበረው በሳይንስና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ነበር፡፡ የዚህ ጋዜጣ አዘጋጅና ባለቤት ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ መሸሻ ሲሆን በ2005 ዓ.ም ጋዜጣው በወቅቱ ከኅትመት ውጭ ሲሆን ዋና አዘጋጁ/ባለቤቱ “በቀጥታ ባያግዱኝም በማተሚያ ቤቶች በኩል እንዳላሳትም አድርገውኛል፤ ምን አልባትም መንግሥት ሳይሆን አይቀርም” በማለት ጥርጣሬ እንደነበራቸው ያገኘናቸው ምንጮች ይናገራሉ፡፡

አዲስ ነገር ጋዜጣ

አዲስ ነገር ጋዜጣ በመስከረም 1999 ዓ.ም መታተም የጀመረች ሲሆን በአንባቢያን ዘንድ ዘወትር ቅዳሜ ጠዋት በጉጉት የምትነበበ ሳምንታዊ የአማርኛ ጋዜጣ ነበረች፡፡ በወቅቱ ጋዜጣዋ ያቋቋሟት ስድስት በሳል ጋዜጠኞች ነበሩ፡፡ ሌሎች ልዩ ልዩ ባለሙያዎችም የጋዜጣዋ ተጋባዥ ጸሐፊያን ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡ ጋዜጣዋ ሁለት የአርትዖት ግቦችን የያዘች ነበረች “የህዝብ ምክንያት” እና “የነፃነት እና የነፃነት” መግለጫ በሚል የምትዘጋጅ ጋዜጣ ነበረች፡፡ ጋዜጣዋ ነሐሴ 28 ቀን 2001 በወጣው የጋዜጣው የመጨረሻ እትም ምክንያት በጸረ ሽብር አዋጅ ቁጥር 652/2001 ክስ ሲመሰረትባት አዘጋጆች ሃገር ለቀው በመሰደዳቸው ምክንያት ኅትመቷ ተቋረጠ፡፡ አዲስ ነገር ጋዜጣ በኢትዮጵያ የኅትመት መገናኛ ብዙሃን ታሪክ ውስጥ ተወዳጅ የነበረች ጋዜጣ ስትሆን በጠንካራ የሚዲያ ባለሙያዎች ልዩ ጥንቃቄና በእውቀት ተዘጋጅታ ለአንባቢያን ትደርስ ነበረ፡፡

ሰንደቅ ጋዜጣ

ሰንደቅ ጋዜጣ ነሐሴ 1997 ዓ.ም ጀምሮ በየሳምንቱ ረቡዕ በመታተም ለ14 አመታት ያህል ለአንባቢያን ስትደርስ የቆየች ጋዜጣ ናት፡፡ ጋዜጣዋ በታዋቂው ኢትዮጵያዊ ባለሃብት በሼህ መሐመድ አሊ አላሙዲን የገንዘብ ድጋፍ ይደረግላት እንደነበር መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ ሰንደቅ ጋዜጣ በኅትመት ላይ በቆየችበት የሥራ ዘመን በአንዳንድ ይዘቶች ምክኒያት ክስ ቀርቦባት የነበር ቢሆንም በጊዜው ከፍ እያለ በመጣው የወረቀትና የኅትመት ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ ነሐሴ 10፣ 2010 ዓ.ም ጋዜጣዋ መዘጋቷን ወቅቱ አዘጋጆች ተናግረዋል፡፡

ፍትሕ መጽሔት

ፍትህ መጽሔት የሕትመት ውጤቶች እጅግ በተዳከሙበት ወቅት በ2008 ዓ.ም በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የተመሰረተ ነፃ ጋዜጣ ሲሆን በይዘቱ ወቅታዊና ኹነኛ መረጃዎችን ተንትኖ ለአንባቢያን በማድረስ ትታወቅ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ከ2008 እስከ ሐምሌ 2011 ባለው ጊዜ በታተሙ ርእሰ ጉዳዮች ምክኒያት አዘጋጆቹ 41 ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡ ክሱ የተመሰረተውም ነሐሴ 2011፣  የካቲት 2012 ፣እና መጋቢት 2012 ላይ ታትመው በወጡት መጣጥፎች መንግስትን በመቃወም እና የወጣቶች ተቃውሞን አስመልክቶ ባሰፈረው ጽሑፍ ምክኒያት እንደነበር መረጃች ያሳያሉ፡፡ ፍትህ መጽሔት ሐምሌ 2012 ዓ.ም የመጽሔቱ ሽፋን በሰጠው ጽሑፍ “የሃገሪቱን ብሄራዊ ደህንነት የሚጎዳ” ሆኖ ተግኝŸል በማለት በመንግሥት ትእዛዝ ተዘግቷል ይላል መረጃው፡፡

አውራምባ ታይምስ

አውራምባ ታይምስ በነሐሴ 2007 ዓ.ም በጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ አዘጋጅነት በአማርኛ ቋንቋ ይዘጋጅ የነበረ ሳምንታዊ የግል ጋዜጣ ነው፡፡ የዚህ ጋዜጣ አዘጋጅ ዳዊት ከበደ ከዚህ በፊት ሀዳር የተሰኘ የኅትመት ውጤት ያሳትም የነበረ ሲሆን ከሌሎች ጸሐፊዎችና አዘጋጆች ጋር ይቀርቡ የነበሩት ጽሑፎች እና ርዕሰ ጉዳዮች ጋዜጣውን በሳል ጋዜጣ እንዳስባላት ይነገራል፡፡ ጋዜጣው ከወቅታዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ባለፈ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን እያዋዙ የሚያቀርቡ በቋንቋ እና ፎክሎር የተካኑ ዘጋቢዎች፣ የዩንቨርስቲ መምህራን፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን እንግዳ በማድረግና በአምደኝት ያሳትፍ ነበረ፡፡ አውራምባ ታይምስ በድፍረት በሚያነሷቸው ጉዳዮችና ይዘቶች የጋዜጣው ሽፋን በገዢው ፓርቲ አባላትና ተባባሪዎቻቸው ላይ የተቀነባበረ የስም ማጥፋት ዘመቻን አስከትሏል ተብሎ ተፈርጇል፡፡ አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ “በሀገሪቱ የአረብ ጸደይ አይነት አመፅ ለመቀስቀስ ሞክሯል” በሚል ክስ ሲመሰረትበት የጋዜጣው አሳታሚዎች የመታሰር እና የመሰደድ ችግር ሲገጥማቸው የጋዜጣው ሕትመት ተቋርጦዋል፡፡

ይቀጥላል

ምንጭ

ልዩ ልዩ ሰነዶች

የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በኢትዮጵያ Voice of America (VOA)

Previous article

You may also like

Comments

Comments are closed.