ማኅበራት/ MIRH/ 30 መጋቢት 2022
በፍቃዱ አለሙ
መግቢያ
ሚዛን የጋዜጠኞች ሞያ ምሩቃን ማኅበር
መግቢያ
ሚዛን የጋዜጠኞች የሙያ ምሩቃን ማኅበር ሲሆን በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጀቶች ባለሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሠረት ነሐሴ 13/2013 ዓ.ም ሕጋዊ የምስክር ወረቀት አግኝቷል፡፡ "ሚዛን" የጋዜጠኞች የሙያ ማኅበር የተለየ የሚያደርገው የጋዜጠኝነትን ሞያ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ተምረው በዘርፉ የትምህርት ማስረጃው/ዕውቅና/ ያላቸውን ጋዜጠኖችና ምሁራን አባላት ያካተተ መሆኑ ነው፡፡ የተመሠረተው በአምስት/5/ መሰራች አባላት ሲሆን፣ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ አስራ አምስት /15/ ፤የማህበሩ ቋሚ አባላት ብዛት ሰላሳ /30/ ናቸው።
ራዕይ
የኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት ሞያ ከሚፈለገው ነጻነትና ክብር እንዲደርስ ማድረግ
ግብ
በ2023 ዓ.ም ሚዛን የጋዜጠኞች ሞያ ምሩቃን ማህበር ከምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የሞያ ማህበር እንዲሆን ማስቻል ነው።
ዓላማ
የማኅበሩ መቋቋም ዋና ዐላማ የሞያው ክብር እንዲጠበቅ ማድረግና ሞያና ሞያተኛው እንዲገናኙ ማስቻል ነው፡፡
ዝርዝር የማኅበሩ አላማዎች የሚከተሉት ናቸው፤
- በመንግስትና በህብረተሰቡ በኩል ለሞያው ያለውን የተዛባ አመለካከት እንዲቀየር ንቃት መፍጠር፣
- የሞያውክብርእንዲጠበቅ ማድረግ፣
- በተለያዩየመገናኛብዙሃን የሚሰሩ ግለሰቦችን ሞያውን ያለ ሞያቸው በሚሰሩት ስህተት፣ ምክንያት ገጽታውን እንዲበላሽ በማድረግ የሚሰሩትን ስህተት እንዲስተካከል ምክረ ሀሳብ ማቅረብ፣
- በከፍተኛትምህርትተቋማት የጋዜጠኝነት ትምህርት አሰጣጥን የተስተካከለ እንዲሆን ሞያዊ ምልከታ ማድረግ/ ለምሳሌ አካታችነት/ Inclusiveness/፣
- እና ሌሎች
የወደፊት ዕቅድን በተመለከተ
ይህ ማህበር ስኬታማ ሲሆን ለወደፊቱ እንደ ዕቅድ ከያዛቸው ውስጥ የራሱ የሆነ የብርድካስት ሚዲያ እንዲኖረው ይሰራል፡፡
- እንዲሁም በተለያዩ ማህበራዊ ኩነቶች ላይ በየሶስት ወርና ሰድስት ወር የሚዘጋጅ መጽሔት ይኖረዋል፡፡
- የጋዜጠኞች የደመወዝ እንዲስተካከል ይታገላል
- የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ የመናገር ፣ የማተም መብት፣የመንቀፍ መብት እና የመዘገብ መብት ይህ የረዥም ጊዜ የትግል ውጤት እንዲቀጥል ማህበሩ ጉልህ ሚና ይጫወታል
- የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ለባለሞያው/ለጋዜጠኞች የሚሰጡትን የህግ ከለላ እንዲጎለብት እናደርጋለን
- የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ለሞያው ክብር የሚደረገውን ትግል እንዲደግፍና የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ሞያተኛው በተገቢው ቦታ እንዲቀመጥ ቁጥጥር እንዲያደርግ ጥረት እናደርጋለን፡
- የኢ.ፌ.ዴ.ሪየሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን/F.D.R.E. Authority of Civil Society Organizations) ፣ በሞያው ፍቃድ ሲሰጥ የሞያ ቁጥጥር እንዲያደርግ እናደርጋለን፡፡
ጋዜጠኝነት ሞያ ነው!
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበር
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበር (ኢጋማ)
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበር (ኢጋማ) በ1969 ዓ.ም. ተመሠረተ::
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያ ሴቶች ማኅበር
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያ ሴቶች ማኅበር
አድራሻ፡- https://www.facebook.com/Ethiopian-Media-Women-Association-EMWA-277560039073115/
ኢሜል፡- ethiopianmwa@gmail.com
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር በቀድሞው የኢትዮጵያ ሲቪክ ማኅበራት ኤጀንሲ በ2012 ዓ.ም በሕጋዊ መንገድ ተመሠረተ። ሲመሰረት በአምስት ጋዜጠኞች አማካኝነት ነበር፡፡
ማህበሩ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን፤ ማለትም የዜና እና የካሜራ ባለሙያዎችን ያቀፈ ማህበር ነው፡፡
ማህበሩ ከ130 በላይ የተመዘገቡ አባላትና በቴሌግራም የማህበራዊ ሚዲያ አማካኝነት የሚገናኙ ከ1,300 በላይ አባላት አሉት፡፡
ማህበሩ ጋዜጠኞች፣ ዜና አንባቢዎች፣ የትርፍ ጊዜ ጋዜጠኞች፣ የፎቶግራፍ ጋዜጠኞች እና በጋዜጠኝነት ሙያ ዙሪያ ያሉ ባለሙያዎችን በአባልነት ይዟል፡፡
ለትርፍ ያልተቋቋመው ማህበሩ የፕሬስ ነፃነትን የማስፋፋት፣ እንደ አለም አቀፍ የጋዜጠኝነትና ጋዜጠኞች ማህበራት ጋዜጠኞች ያለፍርሀትና ደህንነታቸው ተጠብቆ ስራቸውን የማከናወን መብታቸውን የማስጠብቅ እና ሥነ ምግባራዊ ጋዜጠኝነት እንዲሰፍን የማበረታታት ከፍተኛ ፍላጎት አለው።
ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫዎች፡-
- በመገናኛ ብዙሃን ውስጥ የሚገኙ ባለሙያዎችና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ናቸው፡፡
- ለጋዜጠኞች ስጋት የሚሆኑ ጉዳዮችን መታገልና ለሙያተኞች ዘብ መቆም
- ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና ለአጠቃላይ የሚዲያ ኢንዱስትሪው የስልጠና እና የማማከር አገልግሎት መስጠት
- በፈጠራ የታጀበ፣ ስነምግባር ያለው እና ኃላፊነት የሚሰማው የተሻለና ሙያዊ ክህሎት የተሞላበት ምልከታ ያለው የዜና ክፍል አመራር፣ ባህል እና ብዝሃነትን ማዳበር።
- ሚዛናዊ ዘገባና መረጃ ማረጋገጥ
- ለህዝብ ነፃ የመረጃ ፍሰት መሟገት
- የንግድ ማኅበራት መርሆዎችን እና አደረጃጀቶችን ጥበቃ እንዲደረግላቸው ማድረግ፣ መከላከል እና ማስተዋወቅ
- ሙያዊ ችሎታን ለመጠበቅ እና ለማሻሻል፣ ከፍተኛ የጋዜጠኝነት ደረጃዎችን፣ የጋዜጠኝነት ሥነ-ምግባር እና የጋዜጠኝነት ትምህርትን ማሳደግ
እስካሁን ያከናወናቸው ተግባራት፡-
- ስልጠና፣
- የማማከር አገልግሎት፣
- ወርሀዊ የሚዲያ ዳሰሳ እና ግምገማ፣
- መግለጫዎችን ማውጣት፣
- መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ትብብር መፍጠር፣
- ለማህበሩ መስራቾችና ለቀድሞ ስራ አስፈፃሚ አባላት እውቅናና ሽልማት መስጠት።
ራዕይ፡-
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር ነጻ፣ ለመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ዘብ የሆነ ለትርፍ ያልተቋቋመ ማህበር ነው፡፡ የዳበረ የጋዜጠኝነት ስነምግባርና እድገት የማየት ብሎም ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እና የሚዲያ ገጽታን የመደገፍ ራዕይ አለው፡፡
አድራሻ፡- 091 267 5637
የአማራ ክልል ጋዜጠኞች ማኅበር
መግቢያ
የአማራ ክልል ጋዜጠኞች ማህበር በጋዜጠኝነት ሙያ በተመረቁ ጋዜጠኞች አማካኝነት በ2005 ዓ.ም. የተቋቋመ ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ የመንግስት፣ የግልና የማህበረሰብ የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎችን በአባልነት ይዟል፡፡ ከ760 በላይ አባላት ያሉት ማህበሩ ለውጭ መገናኛ ብዙሀን የሚሰሩ ጋዜጠኞችንም አካቷል፡፡
ራዕይ፡
- በሚዲያ ዘርፉ ሰላምን ለማስጠበቅ በክልሎችና ማህበረሰቡ መሀከል መልካም ግንኙነት እንዲኖር የሚሰሩ ነጻ ጋዜጠኞች ተፈጥረው ማየት
- ለማህበረሰቡ መረጃ፣ አስተማሪ ነገሮችንና መዝናኛዎችን በማቅረብ ለባህልና ለማህበራዊ ኑሮ እድገት የድርሻውን መወጣት
- ታማኝና ሳቢ መረጃዎችን፣ በማቅረብ እድገትና ዲሞክራሲን ማሳደግ
ተልእኮ:
- የማህበረሰቡን ፍላጎት ለማሟላት የሚጥር ነጻና ብርቱ ሚዲያ እንዲኖር ማድረግ
- መረጃን ለሁሉም ዜጋ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ
- በእኩልነትና በባህል ልዩነት ላይ በተመሰረተች ሀገር፤ ሰላማዊና የበለጸገች ሀገርን ለመገንባት፤ ማህበራዊ፣ ባህላዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚኖሩ መረጃዎችንና ውሳኔዎችን በክልልና ሀገር አቀፍ ደረጃ በነጻነት መለዋወጥና መነጋገር እንዲቻል ማድረግ
ዋና ዋና ተግባራት:
- ስልጠናዎችን በመስጠት የጋዜጠኞችን አቅም መገንባት
- ከሚዲያ ጋር የተያያዙ ጥናትና ምርምሮችን ማድረግ
- የኢትዮጲያ ሚዲያን በሚመለከት በአመት ሁለቴ በኢንተርኔት እና መጽሄት ማሳተም
- ለጋዜጠኞች መብት መቆም
- አመታዊ ብሄራዊ የሚዲያ ጥናትና ምርምር ማዘጋጀት
አድራሻ፡
+2519 18718307
የኦሮሚያ ጋዜጠኞች ማኅበር
ምስረታ፡
የኦሮሚያ ጋዜጠኞች ማህበር በ2006 ዓ.ም. በወጣት ጋዜጠኞች አማካኝነት የተቋቋመ ማህበር ነው፡፡ በዋነኝነት በኦሮሚያ ክልል ሚዲያዎች፣ እንደሀገር ደግሞ በሀገሪቱ የሚዲያ ዘርፍ እድገት ላይ የድርሻውን መወጣትና ለውጦችን ማገዝ የማህበሩ መነሻ ነው፡፡
በሚዲያ ዘርፉ ውስጥ ሙያዊነትን(professionalism) ማጎልበት፣ የዲሞክራሲ እድገትን ማፋጠንና ጥሩ አስተዳደር መኖሩን ማረጋገጥ፣ የመገናኛ ብዙሀንን በመጠቀመ እድገትን መደገፍ የማህበሩ ዋነኛ አላማዎች ናቸው፡፡
አወቃቀር፡
ከማህበሩ አባላት የሚውጣጣው ጠቅላላ ጉባኤ የኦሮሚያ ጋዜጠኞች ማህበር የበላይ አካል ነው፡፡ የዳይሬክተሮች ቦርዱ ጠቅላላ ጉባኤው በሚመርጣቸው የካበተ ልምድ ባላቸው፣ የትምህርት ደረጃቸው ከፍ ባሉና የተለያየ ልምድ ባላቸው ግለሰቦች የሚቋቋም ነው፡፡ እናም ቦርዱ ለማህበሩ ስትራቴጂካዊ የአመራርነት ሚናን ይጫወታል፡፡
ራዕይ፡
የኦሮሚያ ጋዜጠኞች ማህበር ራዕይ፤ በ2022 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ነጻ እና ፍትሀዊ ሚዲያ፣ ሀላፊነት የሚሰማውና ብቁ ባለሙያ ብሎም ከፍ ያለ ግንዛቤ ያለው ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት ነው፡፡
ተልዕኮ፡
በኦሮሚያና በሌሎችም ክልሎች የሚገኙ የሚዲያ ባለሙያዎች በእውቀት የካበቱ፣ ሀላፊነት የሚሰማቸውና፤ አቅምን በማጎልበት እና ልምድና ቴክኖሎጂን በማካፈል የእድገት መሪዎች ማድረግ የማህበሩ ተልዕኮ ነው፡፡
አባላት፡
በአሁኑ ወቅት የኦሮሚያ ጋዜጠኞ ማህበር ከ350 በላይ የተመዘገቡ አባላት ያሉት ሲሆን አባላቱም ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ ናቸው፡፡
አድራሻ፡
https://oromiajournalists.com/
https://www.facebook.com/ojournalists/
ናዚፍ ጀማል፤ ፕሬዝዳንት
+251911234266
የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ሬዲዮ ብሮድካሰተር ማኅበር
የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ሬዲዮ ብሮድካሰተር ማኅበር
አድራሻ፡-
https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=130718552962232&id=110688858298535
ስልክ ቁጥር፡- +251 911 791 925
+251 913 209 322
የኢትዮጵያ አርታእያን ማኅበር
የኢትዮጵያ አርታእያን ማኅበር
https://www.facebook.com/Etheditorsguild/
Email address:- editorsethiopia@gmail.com
የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር
የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር
የኢትዮጵያ ባሕልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማኅበር
የኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማህበር በኢትዮጵያ ታሪክ፣ ተፈጥሮ፣ ቅርስ፣ ባህልና እሴት ዙሪያ የሚሰሩ ጋዜጠኞች የሙያ ማህበር ነው፡፡ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት የካቲት 15 ቀን 2013 ዓ.ም በመዝገብ ቁጥር 5461 በማህበራት ማደራጃ እውቅናና ህጋዊ ሰውነትን ያገኘ ማህበር ነው፡፡
ከስራው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ካላቸው የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ የቅርስ ጥበቃ ባስልጣን እና የዱር እንስሳት ጥበቃ ባስልጣን፣ በትብብርና በአጋርነት ከማህበሩ ጋር እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጲያ ባህልና ቱሪዝም ጋዜጠኞች ማህበር የኢትዮጲያ ፕረስ ካውንስል አባልም ነው፡፡
በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ጋዜጠኞች የማህበሩ አባላት ሲሆኑ በቁጥር 36 ይደርሳሉ፡፡ እነኚህ አባላቱ ከአዲስ አበባ ውጪ በጋምቤላ፣ ባህር ዳርና ሐረር ከተሞች የሚገኙ ናቸው፡፡
አላማ፡
- የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲለዩ፣ እንዲለሙ፣ እንዲተዋወቁና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲኖራቸው ማድረግ
- የተፈጥሮ መስህቦች በሰው ሰራሽ ጫና፣ በፖሊሲ ውስንነትነሰ ትኩረትበመነፈግ የሚደርስባቸው ውድመት እንዲቀንስ አካባቢ ጥበቃ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ
- ወጣቶች፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ ያደረገና የስራ እድል የሚፈጥር ቱሪዝም ልማትና ባህል ኢንዱስትሪ እንዲያድግ ማስቻል
የሚያከናውናቸው ተግባራት፡
- ሴት የቱሪዝም ጋዜጠኞችን ብቃት ለማሳደግ ይንቀሳቀሳል
- የቱሪዝም ኢንዱስትሪው ለሴቶች የሚኖረው ጠቀሜታ ላይ ይሰራል
- ቱሪዝም ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እንዲሆን ይሰራል
አድራሻ፡
+251 984 1443 78
+251 954 8809 35
የኢትዮጵያ ኢንቫይሮመንታል ጋዜጠኞች ማኅበር
የኢትዮጵያ ኢንቫይሮመንታል ጋዜጠኞች ማኅበር
የማህበረሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ በኢትዮጵያ ዘላቂ እድገትን ለማምጣት ፍላጎቱ የነበራቸው ልምድ ያካበቱ የሚዲያ ባለሙያዎች ከፋኖስ ኢትዮጵያና የጀርመኑ ሄንሪች ቦል ፋውንዴሽን ባገኙት ድጋፍ በ1998 ዓ.ም. ማህበሩን አቋቋሙ፡፡
ማህበሩ የመንግስት፣ የግል እና አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ውስጥ የሚሰሩ 47 ባለሙያዎችን በአባልነት የያዘ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ማህበሩ መዝለቅ የቻለው እስከ 2004 ዓ.ም. ብቻ ነው፡፡
የኢትዮጵያ በጎ ፈቃደኛ ጋዜጠኞች ማኅበር
የኢትዮጵያ በጎ ፈቃደኛ ጋዜጠኞች ማኅበር
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ጋዜጠኞች ማኅበር
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ጋዜጠኞች ማኅበር
የኢትዮጵያ ናሽናል ሚዲያ ሰፖርት
ኢትዮጵያን ናሽናል ሚዲያ ሰፖርት (Ethiopian National Media Support (ENMS) ለትርፍ ያልተቋቋመ ሀገር በቀል ድርጅት ሲሆን በሙያው በተካኑ ጋዜጠኞች፣ ፕሮፌሰሮች፣ የጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን አስተማሪዎች እና ተመራማሪዎች የተመሠረተ መንግሥትታዊ ያልሆ ተቋም ነው፡፡
የኢናሚሳ (ENMS) ዓላማ በሀገር ውስጥ ለሚገኙ ጋዜጠኞች፣ የሚዲያ ተቋማት፣ የሙያ ማኅበራት እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚዲያ እድገት ዙሪያ በጋራ የሚሰሩበትን የትብብር ማእቀፍ መፍጠር ነው፡፡
በዚህ ሂደትም የዘርፉ ተዋንያን እርስበርሳቸው ያለባቸውን ክፍተት በጥናት በመለየትና በትብብር የሚሰሩበትን አቅጣጫና የመፍትሄ ሃሳብ በማሳየት ከዘርፍ የሚጠበቀውን አስተዋጽኦ እንዲያበርክቱ ማስቻል ነው፡፡
ራዕይ
በኢትዮጵያ በሙያው የታነጹ፣ ነጻ እና ኅብረተሰቡን በትጋት የሚያገለግሉ የብዙኃን መገናኛ ተቋማትና የዘርፉ ባለሙያዎች ተፈትረው ማየት፣
ተልእኮ
ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች፣ የብዙሃን መገናኛዎች፣ የጋዜጠኛ ማኅበራት፣ እንዲሁም የጋዜጠኝነት ትምህርት ቤቶች የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ኃይል ሆነዉ እንዲያገለግሉ መደገፍ እና ማጠናከር፣
ግብ
በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን የዲሞክራሲእና ሃገራዊ ግንባታ ጉዞ በንቃት የሚደግፉ ጠንካራ የብዙሃን መገናኛዎች እንዲፈጠሩ እገዛ ማድረግ፣
አድራሻ
አዲስ አበባ፣ ካዛንቺስ፣ ኢትዮጵያ
0911640449
0913141229
የትግራይ ጋዜጠኞች ማኅበር
የትግራይ ጋዜጠኞች ማኅበር
የሶማሊ ክልል ጋዜጠኞች ማኅበር
የሶማሊ ክልል ጋዜጠኞች ማህበር
የሶማሊ ክልል ጋዜጠኞች ማህበር በጅግጅጋ ከተማ መስከረም 9 ቀን 2014 ዓ.ም ተመሰረተ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር
የደቡብ ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር
የደቡብ ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር በደቡብ ኢትዮጵያ ያሉ ጋዜጠኞችን ለማደራጀትና የፕረስ ነጻነትን ለማስጠበቅ ያለመ መንግስታዊ ያልሆነና ለትርፍ ያልተቋቋመ ማህበር ነው፡፡
በ2014 ዓ.ም የተቋቋመው ማህበሩ የጋዜጠኝነት ፍላጎቱ ያላቸው የህትመት፣ የሬዲዮና ቴሌቪዥን፣ ብሎም የበይነመረብ ጋዜጠኞችን፣ የጋዜጠኝነት መምህራንና ተማሪዎችን በአባልነት የያዘ ነው፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር በደቡብ ክልል፣ ሲዳማ ክልል እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ 17 የመገናኛ ብዙሃን ውስጥ የሚሰሩ 2,400 ባለሙያዎችን ይወክላል፡፡
የሚያከናውናቸው ተግባራት፡-
የደቡብ ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር ጋዜጠኝነትን ለመደገፍና መገናኛ ብዙሃን በዘላቂነት ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር አቅም እንዲኖራቸውና የህብረተሰብ ህይወት ላይ ተጽዕኖ ያላቸውን ነገሮች የማሳወቅ ስራ እንዲሰሩ የድጋፍ ስራ ይሰራል፡፡
ስለነገሮች በቂ መረጃ ያለው ዜጋ ለመፍጠር ነጻ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ያበረታታል፤ ተተኪ ጋዜጠኞችን የማነቃቃትና የማስተማር ስራ ይሰራል፤ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽና ለፕረስ ነጻነት ብሎም ለጋዜጠኞች ድምጽ ዘብ ይቆማል፡፡
ማህበሩ በተለያዩ ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች የጋዜጠኝት ሙያን ለመጠበቅና ለማሻሻል ይጥራል፡፡ በሚያዘጋጃቸው መድረኮች የመጻፍ፣ የመዘገብ እና የማረም እንዲሁም የስነምግባር እና የመረጃ ነፃነት በሰፊው ይዳሰሳሉ፡፡
ጋዜጠኞች በከፍተኛ ስነ-ምግባር እና ውሳኔ አሰጣጥ እንዲሁም የአባላት ግንኙነትን አክብረው ስራቸውን እንዲያከናውኑ ማህበሩ ይተጋል፡፡
አድራሻ፡-
ስልክ ቁጥር፡- +251933575345
ኢሜል፡- Southethiommpa@gmail.com
Comments