የግል መገናኛ ብዙሃን ፕሮፋይል

ኢትዮጲያን ቢዝነስ ሪቪው – ኢቢአር

የግል መገናኛ ብዙሃን ፕሮፋይል / MIRH/ 23 መስከረም 2015

በመቅደስ ደምስ

በኢትዮጵያ ሚዲያ ባለስልጣን መዝገባ ቁጥር 227/2004 እና በኢትዮጵያ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፍቃድ ቁጥር MT/AA/2/0011632/2004 የተመዘገበው ኢትዮጲያን ቢዝነስ ሪቪው፤በታዋቂ ምሁራን፣ የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች እና ከፍተኛ ጋዜጠኞች የተፃፉ እና በጥናት ላይ የተመሰረቱ ይዘቶችን በማዘጋጀት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚታተም ወርሃዊ መፅሄት ነው።

የግሉ ሴክተርን ለማስተዋወቅ እና በፖሊሲ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር እንደ ንግድ አመራር፣ ሥራ ፈጣሪነት ወይም ኢንተርፕራይዝ ልማት፣ የግብይት ስትራቴጂ፣ ድርጅታዊ ለውጥ፣ የሰው ካፒታል፣ ዓለም አቀፍ ንግድ፣ ፋይናንስ፣ ታክስ፣ ጉምሩክ፣ ፖሊሲ፣ ቴክኖሎጂ እና የንግድ ህግን እና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች በመጽሄቱ ይዳሰሳሉ፡፡

በኢትዮጵያ ተመራጭ የቢዝነስ መፅሄት መሆንን ራዕዩ ያደረገው መጽሄቱ፤ በጥናት ላይ የተመሰረተ የግሉ ዘርፍ ልማትን የሚያበረታታ ይዘት ማቅረብ ደግሞ ተልዕኮው ነው።

የቻምፒዮን ኮሙዩኒኬሽንስ ዋነኛው ኅትመት የሆነው ኢቢአር፤ በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ በሰብስክሪፕሽን (subscription)፣ እንዲሁም በዋና ዋና ሱፐርማርኬቶች እና የመጻሕፍት መደብሮች በስፋት ይሰራጫል። በዲጂታል መንገድ ደግሞ በድህረ ገጽ፣ ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ቴሌግራም እና ሊንክድኢን አንባቢያንን ይደርሳል፡፡

አድራሻ፡

በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚኖረውን ግንኙነት እንዲሁም በተናጠል የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች የሚገዛ የአሰራር ሥርዓት ቃል ኪዳን

Previous article

የምርጫ ማስፈጸሚያ ቁሳቁሶችና እና ሰነዶች ድልድል፣ ሥርጭት፣ አጠቃቀም፣ ርክክብና አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 8/2013

Next article

You may also like

Comments

Leave a reply