አፍሪካ

አፍሪካ በመገናኛ ብዙኃን የቢዝነስ ዘገባ ዉስጥ

አፍሪካ/ MIRH/ 09 ሰኔ 2022

በ  Jamlab Africa

Africa No Filter የተሰኘ ተቋም አፍሪካዊያን መገናኛ ብዙኃን ስለ ንግድ የሚዘግቧቸዉን መረጃዎች ይዘት አህጉሩን እንደ ንግድ እና ኢንቨስትመንት መዳረሻ ከማሳየት አንፃር ያላቸዉን የገፅታ  ግንባታ ሚና የተመለከተ ጥናት አድርጓል፡፡ ተቋሙ በዚሁ ጥናቱ አፍሪካን እንደተመራጭ የንግድ መዳረሻ በማሳየት ረገድ በተዘዋዋሪ ተፅእኖ የሚፈጥሩ የዜና እና የመረጃ ክፍተቶችንም ዳስሷል፡፡ በዚህ ጥናት ዉስጥ በ 6000 አፍሪካዊያን እና 183000 ከአፍሪካ ዉጪ የሚገኙ የዜና ድረ ገፆች እ.ኤ.አ ከ 2017 እስከ 2021 ድረስ የተዘገቡ 750 ሚሊየን ያህል ዘገባዎች የተዳሰሱ ሲሆን ዋና ዋና ድምዳሜዎቹ እንደሚከተለዉ ይጠቃለላሉ፡-

  1. አሉታዊ ዘገባዎች– በዓለምአቀፍ ሚዲያዎች ከሚፃፉ ዘገባዎች ዉስጥ አብዝኃኞቹ የአፍሪካን የንግድ እንቅስቃሴ በአሉታዊ መልኩ የሚያስቀምጡ ናቸዉ፡፡ አፍሪካዊያን የዜና ድረ ገፆች በዘገባቸዉ ዉስጥ ለሙስና የሚሰጡት ትኩረት ከአለምአቀፍ ድረ ገፆች ጋር ሲነፃፀር በእጥፍ የበለጠ ነዉ፡፡
    አፍሪካ እና የምእራብ ዓለም ሐገራት-በአለም አቀፍ ድረ ገፆች ስለ አፍሪካ ከተዘገቡ ዜናዎች ዉስጥ 70 በመቶ ያህሉ ከዉጪ ሃይላት (ቻይና፣ አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታንያ፣ ወ.ዘ.ተ)ጋር በተገናኘ የቀረቡ ናቸዉ፡፡
    ዉስን የአፍሪካ ሐገራት፡ በአፍሪካ ንግድ እና ኢንቨስትመንትን በተመለከተ ደቡብ አፍሪካ እና ናይጀሪያ ከሌሎች ሀገራት በበለጠ ሽፋን ይሰጣቸዋል፡፡
  2. ዉስን ትኩረት ፈጠራ እና መዝናኛ ዘርፍ -ምንም እንኳን እንደ ሙዚቃ እና ሌሎች የመዝናኛዉ ዘርፎች በንግድ እና ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ድርሻ ቢኖራቸዉም ጥናቱ ከዳሰሳቸዉ ዘገባዎች ዉስጥ 1 በመቶ ያህሉ ብቻ የመዝናኛዉን ኢንደስትሪ የተመለከቱ ነበሩ፡፡
  3. የወጣቶች እና ሴቶች ዉክልና ማነስ-በ2017 ጀምሮ ወጣቶች በዜና ዘገባዎች ዉስጥ የሚሰጣቸዉ ሽፋን ከ5 በመቶ በ2021 ወደ 8.1 ቀንሷል፡፡
  4. ቅድሚያ ለመንግስታዊ ጉዳዮች-በ2021 ከቀረቡ ንግድ ተኮር ዘገባዎች ዉስጥ5 በመቶ ያህሉ የመንግስታትን እርምጃዎች እና ፖሊሲዎች መነሻ ያደረጉ ነበሩ፡፡ በተጨማሪም አፍሪካያን የዜና ድረ ገፆች በዋናነት በመንግስት ላይ ያተኮሩ ንግድ ተኮር ዝገባዎችን ያቀርባሉ፡፡ ይሁን እንጂ በአለም ላይ በርካታ ዜጎቻቸዉ ስራ ፈጠራን የተመለከቱ የድረ ገፅ ፍለጋዎችን እንደሚያደርጉ ከሚነገርላቸዉ አስር ዋና ዋና ሐገራት ወስጥ ስድስቱ አፍሪካ ዉስጥ እንደሚገኙ ልብ ይሏል፡፡
  5. አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናይህ ስምምነት 30 ሚሊየን ያህል አፍሪካዊያንን ከድህነት ማዉጣት እና የ68 ሚሊየን ያህሉን ገቢ ማሻሻል እንደሚያስችል የሚጠበቅ ከመሆኑም በላይ በ 2035 የአኅጉሪቷን ገቢ በ450 ቢሊየን ዶላር በማሳደግ ከኤክስፖርት የሚገኘዉን ገቢ በ 560 ቢሊየን ዶላር እደሚጨምር፣ ብሎም የአምራችነት አቅምን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ለዉጥ እንደመሚያመጣ ይጠበቃል፡፡ ሆኖም አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ጉዳይ በዜና ዘገባዎችም ሆነ ምርምር ስራዎች ዉስጥ 1 በመቶ ያህል ብቻ ቦታ ተሰጥቶታል፡፡

JAMLAB AFRICA- https://jamlab.africa/

አእምሮ ጋዜጣ

Previous article

ባንዲራችን ጋዜጣ

Next article

Comments

Leave a reply