የግል መገናኛ ብዙሃን ፕሮፋይል

አዲስ ማለዳ – ዜና ከምንጩ

የግል መገናኛ ብዙሃን ፕሮፋይል / MIRH/ 18 መስከረም 2015

በመቅደስ ደምስ

አዲስ ማለዳ በቻምፒዮን ኮምዩኒኬሽንስ አማካኝነት ከጥቅምት 24 ቀን 2011 ጀምሮ የህትመት ገበያውን የተቀላቀለች ሳምንታዊ ጋዜጣ ናት፡፡

ጋዜጣዋ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሚድያ ባለሥልጣን በመዝገብ ቁጥር 241/2010 የተመዘገበች ስትሆን፤ አሳታሚዋ ቻምፒዮን ኮምዩኒኬሽንስ ደግሞ በታህሳስ 2010 ተመሥርቶ በኢፌዴሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በንግድ ፈቃድ ቁጥር MT/AA/2/0011632/2004 የተመዘገበ ነው፡፡

አዲስ ማለዳ በአማርኛ፣ በAfaan Oromoo እንዲሁም በ Af Soomaali ቋንቋዎች በየሳምንቱ ቅዳሜ ለአንባቢያን ትደርሳለች፡፡ በወቅታዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ዜና፣ ትንታኔ፣ ሐተታ እና ቃለ መጠይቅ ለአንባቢያን ታደርሳለች። በዋና ዋና የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ የቀረቡ ነጻ ሐሳቦችንም ታካትታለች።

ጋዜጣዋ በኢትዮጵያ ውስጥ የሊበራል አስተሳሰቦችን እንዲሁም ዴሞክራሲን ለማጎልበት እንደ ሚዲያ የበኩሏን ድርሻ በመወጣት ላይ ትገኛለች፡፡

አዲስ ማለዳ ከጋዜጣው ባሻገር በዲጂታል ሚዲያ መድረኮች በፌስቡክ፣ ዩቲዩብ፣ ትዊተር፣ ቴሌግራም እና ድረ-ገፅ ላይ በንቃት እየሠራች ትገኛለች።

ታማኝ፣ ተመራጭ፣ ዓለም ዐቀፍ ደረጃዋን የጠበቀች፣ እንዲሁም እንደ ሚዲያ በኢትዮጵያ የአራተኛ መንግሥት ሚና የምትወጣ ነፃ፣ ገለልተኛ እና ተማኝ የመገናኛ ብዙኀን መሆን ደግሞ የጋዜጣዋ ራዕይ ነው።

ዋና ዓላማ

  • በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሆነ ተጽዕኖ ፈጣሪ የመገናኛ ብዙኀን ተቋም መገንባት።

አድራሻ፡

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን

Previous article

የመገናኛ ብዙሃን እና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ የስነ ምግባር እና አሰራር መመሪያ ቁጥር 02 /2013

Next article

You may also like

Comments

Leave a reply