የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን ፕሮፋይል

ነጋሪት ጋዜጣ (Negarit Gazeta)

ነጋሪት ጋዜጣ ፕሮፋይል / MIRH/ 02 ሚያዚያ 2015

በሳሙኤል አሰፋ

መገናኛ ብዙሃን ከዘመን ጋር ዘምነው በተለያዩ እድገት ደረጃዎች አልፈው የ21ኛው ክ/ዘ አሰራር ላይ ከመድረሳቸው አስቀድሞ ዘመኑን በሚመጥን ሁኔታ ሰዎች ሃሳባቸውን የሚለዋወጡባቸው የተለያዩ የግንኙነት መሳሪያዎች ነበሩ፡፡ ከእነዚህ የግንኙነት ሳሪያዎች አንዱ ነጋሪት ነው፡፡

ነጋሪት ከመገናኛ አውታር (Communication Medium) ከመሆን በተጨማሪ ለሙዚቃ መሳሪያነትም ያለገለ ቢሆንም፤ የመገናኛ ብዙሃን አማራጮች ባልተስፋፉበት ዘመን ግን ነጋሪት እንደዋና የመገናኛ ዘዴ ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ ስሪቱ በአብዛኛው ከእንጨት ቢሆንም አልፎ አልፎ ግን ከብረት እና ነሐስ ይሰራ ነበረ፡፡ እንዲህ እንደዛሬው ዘመን ልዩ ልዩ በቴክሎጂ የታገዙ ብዙሀን መገናኛዎች ሳይስፋፉ መንግስታት ለሕዝባቸው መልእክት ሲያተላልፉ ወይም አዋጅ ሲያውጁ የሚጠቀሙት ነጋሪትን ነበረ፡፡

ነጋሪት እንደከበሮ በእጅ ሳይሆን በበትር መሰል አጭር መጎሰሚያ ይመታል፡፡ ነጋሪት እየተጎሰመ ስማ! . . .  ስማ! . . .  ላልሰማህ አሰማ እየተባለ አዋጁ ወይም ወቅታዊው መልእክት ይነገራል፡፡ መልእክቱ ልዩ ልዩ የመንግስት አዋጅ እና መመሪያ ለማሳወቅ፣ የግብር ጥሪ፣ ተላላፊ በሽታ መግባቱን እና ሕዝብ እንዲጠነቀቅ ለማሳሰብ፣ የጠላት ወረራ አደጋ መፈጠሩን እና ሕዝቡ ከመንግስት ጎን በመሰለፍ እንዲከላከል ጥሪ ማድረግን ወይም ሌላም ሊሆን ይችላል፡፡ ነጋሪት አንድ ቦታ ሆኖ ወይም በሰው እና በእንስሳት ላይ ተደርጎ እየተንቀሳቀሰ ሊጎሰም ይችላል፡፡ ከመንግስት የወጣው አዋጅ ብርታት እና አስቸኳይ ሆኖ ሲገኝ በርካታ ሕዝብ እንዲያደምጠው፣ ትኩረት እንዲደረግበት ሕዝቡ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ ከመንደር መንደር እየተወዘዋወሩ ሕዝብ በሚሰበሰብብቻቸው ስፍራዎችና በገበያዎች አዋጅ እንዲነገር ይሰማል፡፡

በታሪክ እንደምንመለከተው የኢትዮጵያ መንግስታት አዋጆችን በሚያስደነግጉበት ወቅት የሚጠቀሙት መንገድ ነጋሪት ጋዜጣ ስለነበር ስያሜው የተገኘው ከነጋሪት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ነጋሪት ጋዜጣ ከተመሰረተበት ከ1934ዓ.ም ጀምሮ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ በደርግ፣ በኢህአዴግ እና አሁንም በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የነጋሪት ጋዜጣን እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡ በመንግስት የሚወጡ አዋጆች የጸኑ የሚሆኑት በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣት ጊዜ አንስቶ እንደሆነ እዛው በነጋሪት ጋዜጦች ፍሬ ጉዳዩን ማግኘት ይቻላል፡፡

በቀደመው ዘመን ነገስታት ብዘት ያለው ቋሚ ሰራዊት ስልለነበራቸው “ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት” ሲባል ወደ ዘመቻ አብረዋቸው ከሚዘምቱን መካከል ገበሬው እና ሌላው ሕዝብ ነበር፡፡ የነጋሪት ድምፅ እና የነገስታቱ አዋጅ ሲሰማ ሕዝቡ ማቄን ጨርቄን ሳይል ያለውን የጦር መሳሪያ እና ስንቁን ይዞ ይከተላቸው ነበር፡፡

ነጋሪት ከግንኙነት (Communication) መሳሪያነቱ በተጨማሪ የሙዚቃ መሳሪያም ነው፡፡ የሙዚቃ መሳሪያዎች የአውታር ወይም የክር፣ የትንፋሽ እና የምት ተብለው ይከፈላሉ፡፡ የምት ሙዚቃ መሳሪያ ተብለው ከሚታወቁት ውስጥ ከበሮ፣ አታሞ፣ ነጋሪት፣ ዲቤ ይመደባሉ፡፡ መሳሪያዎቹ ተመሳሳይ አሰራር ቢኖራቸውም አገልግሎታቸው ግን ልዩ ልዩ ነው፡፡ መሣሪያዎቹ ለሙዚቃ የሚጠቅሙ ቢሆኑም ለመንፈሳዊ አገልግሎት ማለትም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለቅዳሴ፣ ወረብና መዝሙር ሲገለግሉ በእስልምና ሀይማኖት ውስጥም ለመንዙማ እና ነሺዳ ያገለግላሉ፡፡ የአፍሪካ ባህላዊ ዕምነቶች African Traditional Religions ተብለው በሚታወቁት አገር በቀል እምነቶች አምልኮ ሥርዓት ውስጥ ከበሮ ሚናው ከፍ ያለ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የከበሮ አሠራርና አመታት ራሱን የቻለ መንፈሳዊ ትርጉም አለው፡፡ አሰራራቸውን በተመለከተ በአብዛኛው ከእንጨት ሲሆን እንጨቱ ውስጡ ከተቦረቦረ በኋላ ጎድጓዳ ስፍራ እንዲፈጠር ተደርጎ ላዩ በተወጠረ ቆዳ ይሸፈናል፡፡ የተወጠረው ቆዳ ሲመታ ውስጡ ክፍተት ያለው እንጨት ድምጽ ይሰጣል፡፡

ወደ ነጋሪት እንመለስና ለበርካታ ዘመናት ዋነኛ የግንኙነት መሳሪያ በመሆን ሲያገለግል እንደኖረ የታሪክ መዛግብት ከትበውት እናገኛለን፡፡ ታል፡፡ አመታቱ ወይም አጎሳሰሙ የሚያስተላልፈውን መልእክት ብርቱነት እና አስቸኳይነት ያመለክታል፡፡ ለምሳሌ በመንግሥት አካል የሚደረጉ የምት ደረጃዎቸን ያን እንደሆነ 3 ወይም 7 ጊዜ ሲጎሰም የሚያስተላፈው መልእክት የተለያየ ከመሆኑም ባሻገር 14 ጊዜ ከተጎሰመ ደግሞ ከመንግስት የሚተላለፈው መልእክት እጅግ አስቸኳይ እና ጊዜ የማይሰጠው በመሆኑ አድማጮች ፈጥነው ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ በተለይ አደጋ የተከሰተ ወይም ጠላት ሀገርን ሲወር አልያም አደጋ ለማድረስ ዝግጁ መሆኑ ከታወቀ ፈጣን ግብረ መልስ በመስጠት ሁሉም ያለውን የጦር መሳሪያ በመያዝ ጥሪ ወደ ተደረገበት ስፍራ ወዲያ እንዲያቀና ይደረጋል፡፡

ምንጭ

ልዩ ልዩ ምንጮች

ቃለ መጠይቆች

የሚዲያ አጠቃቀም ትምህርት ማሰልጠኛ ሞጁል (Media Literacy Training Module)

Previous article

በአውሮፓ ነባር መገናኛ ብዙኃን ቲክ ቶክን በመጠቀም ብዙ ሺሕ ወጣቶችን እየሳቡ ነው

Next article

You may also like

Comments

Comments are closed.