ይማሩ

ተፈላጊ ጋዜጠኞች እንዴት ያሉ ናቸዉ? ቀጣሪዎች ምን ይፈልጋሉ?

ይማሩ/ MIRH/ 17 ጥር 2022

በዴቪድ ብርወር የተፃፈ 

 

ቀጥሎ የተዘረዘሩት ጥቆማዎች Media Helping Media በተሰኘዉ ድረ-ገፅ ለባለሙያዎች በቀረበ ጥያቄ መሰረት ጋዜጠኞች ሲቀጠሩ እንዲያሟሏቸዉ የሚጠበቁ ነገሮችን የሚያስረዱ ናቸዉ፡፡

የህይወት ልምድ የታከለበት የስነ-ባህሪ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ዲግሪ

ኤሪክ ሉ የተሰኘ የ University of Wollongong ባልደረባ ጋዜጠኛ ለመሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ብቻ በቂ የነበረበት ዘመን እንዳከተመ ያስረዳል፡፡ ኤሪክ እንደሚለዉ ጥቂት ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ብስለት ያላቸዉ እና ሃገራዊም ሆነ አካባቢያዊ ጉዳዮችን ከተለያዩ ጉዳዮች አንፃር ማስተዋል የሚችሉ፣ በጥራት መፃፍ እና መናገር እስከቻሉ ድረስ የጋዜጠኝነት ትምህርት ምሩቅ ባይሆኑም እንኳ ከየትኛዉም የማህበራዊ ሳይንስ ወይም ስነ-ሰብ የትምህርት ዘርፍ የተገኙ ምሩቆች እንደሚመረጡ ይናገራል፡፡

ኤሪክ በአስራ ዘጠኝ ሰባዎቹ ከነበሩት ወጣት ጋዜጠኞች ይጠበቁ የነበሩትን ችሎታዎች ማለትም፤ የማወቅ ጉጉት፣ ነገሮችን የማነፍነፍ ተሰጥኦና አቅም እንዲሁም በበርካታ ጉዳዮች ላይ ዉስን እዉቀት እና መረጃዎች ያሏቸዉ ነገር ግን በየትኛዉም ጉዳይ ላይ የተለየ ዝርዝር እዉቀት የማይጠበቅባቸዉን ጊዜ በማስታወስ እንዲህ ይላል:-

“የመገናኛ ብዙሃን መስፋትን እና ሉላዊነትን መሰረት አድርጎ የተፈጠረዉ ስርዓት ከአካባቢያቸዉ ወጣ ብለዉ ማሰብ የሚችሉ፣ ነገሮችን በተለያየ አቅጣጫ መተርጎም እና መተንተን የሚችሉ፣ ስለ ሁሉም ነገር ጥቂት የሚያዉቁ፣ ስለጥቂት ነገሮች ደግሞ ብዙ መረዳት ያላቸዉ ጋዜጠኞች ይፈለጉ ጀመር፡፡ የጋዜጠኝነት የዩኒቨርሲቲ ዲግሪም እንደ አንድ መስፈርት መቀመጥ ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ከዚህ መስፈርት ጀርባም የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን አስፈላጊዉን የማስተዋል እና የመተንተን አቅም እንደሚይዙ የሚያምን አመክንዮ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን ይህ አመክንዮ ሁል ጊዜ ትክክል ባይሆንም የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ምሩቅ ካልሆኑ ሰዎች የተሻለ መረዳት እና ግንዛቤ ሊኖራቸዉ ቢችልም ከትምህርት ባለፈ የሚያስፈልጉ የባህሪ እና የህይወት ልምዶች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ከዚሁ ጋር አያይዞ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡”

አመለካከት እና ክህሎት 

ለሰለላሳ ሰባት አመታት በጋዜጠኝነት ያገለገለዉ Harishchandra Bhat ከላይ በተቀመጠዉ የኤሪክ ሃሳብ ይስማማል፡፡ የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ብቻዉን በቂ እንዳልሆነ እና የተደራሽን ፍላጎት ያማከለ ዜናን ነቅሶ የመለየት ክህሎት እንደሚያስፈልግም ይናገራል፡፡ የጋዜጠኝነት ትምህርት ሳይወስዱ በሙያዉ ላይ ጉልህ አሻራቸዉን ያሳረፉ ጋዜጠኞችን በመጥቀስም ጋዜጠኝነት የተሰጥኦ እንጂ የልምምድ ሙያ አይደለም ሲል ይከራከራል፡፡

በተመረጡ ጉዳዮች ላይ ጠለቅ ያለ እዉቀት  

Nick Raistrick በመገናኛ ብዙሃን ልማት ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን የጋዜጠኝነት መስፈርቶች እንደምሰራዉ የጋዜጠኝነት አይነት ሊለያዩ እንደሚችሉ እና በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ዘርዘር ያለ እዉቀት ይዞ መገኘት ጠቀሜታ እንዳለዉ ያስረዳል፡፡ በተለይም የቋንቋ እና የስነ-ሰብ ምሩቃን በሰፊዉ በጋዜጠኝነት ተሰማርተዉ እንደመገኘታቸዉ በአንድ የሳይንስ ወይም ሌላ ዘርፍ ላይ ተጨማሪ እዉቀት ያላቸዉ ሰዎች ተፈላጊ ናቸዉ ሲል ያስረዳል፡፡

የታሪክ እና የቋንቋ እዉቀት

Nick Walshe የተሰኘ የመገናኛ ብዙሃን አማካሪ እንደሚለዉ ደግሞ ጋዜጠኛ መሆን የሚፈልጉ ሰዎች በመጀመሪያ አንድ ልዩ ሙያን ካጠኑ በኋላ የጋዜጠኝነት ትምህርትን ቢያገኙ የተሻለ ነዉ ይላል፡፡ በተለይም አለም አቀፍ ጋዜጠኛ መሆን የሚፈልጉ ሰዎች የዉጪ ቋንቋ (አረብኛ፣ ማንዳሪን፣ ራሺያኛ፣ ስዋሂሊ፣ ወይም ፈረንሳይኛ ሊሆን ይችላል) በማጥናት ከጋዜጠኝነት ትምህርት ጋር ቢያቀናጁ ስኬታማ እንደሚሆኑ ኒክ ይመክራል፡፡ በመካለኛዉ ምስራቅ ጋዜጠኛ ሆነዉ ለመስራት የሚያስቡ ሰዎችም ታሪክን በማጥናት በቂ መረዳት እንዲሰንቁ አጥብቆ ይመክራል፡፡ ከታሪክ ወይም ቋንቋ ጥናት በኋላም የጋዜጠኝነት ትምህርትን በማግኘት ሙያዉን መቀላቀሉ የተሻለ እንደሆነ ያስረዳል፡፡

ጉጉት እና አሰላሳይነት

የMedia unlimited ዳይሬክተሯ  Magda Abu-Fadil በጋዜጠኝነት መምህርነትም ሆነ በጋዜጠኝነት ልምዷ የተማረችዉ ነገር ቢኖር  ወጥ የሆነ የጋዜጠኝነት መስፈርት ማስቀመጥ አስቸጋሪ መሆኑን ነው፡፡

“ምንም እንኳን የጋዜጠኝነት ምሩቅ የሆኑ በርካታ ምሩቃን ቢኖሩም ይህ የመስፈርት ሳይሆን የፍላጎት ጉዳይ ነዉ፡፡ ኒክ እንዳለዉ በተለይ ለአለም አቀፍ ጋዜጠኞች የዉጭ ቋንቋ ክህሎትም አስፈላጊ ነዉ፡፡ ለነገሮች ጉጉ መሆን፣ ጉዳይን ከብዙ አቅጣጫ ማስተንተን፣ ትክክለኛነት፣ ፍትሓዊነት፣ ሚዛናዊነት፣ እንዲሁም በየትኛዉም አዉታር ጥሩ መረጃን የማድረስ ፍላጎት እጅግ አስፈላጊ ናቸዉ፡፡” ስትልም ታስረዳለች፡፡

 

ለተጨማሪ ንባብ:

ተፈላጊ ጋዜጠኞች እንዴት ያሉ ናቸዉ? ቀጣሪዎች ምን ይፈልጋሉ?

የመገናኛ ብዙሃን ማሻሻያ ላይ የተነሱ ሃሳቦች

Previous article

የዜና ጉዳይ መረጣ እና ምዘና 

Next article

You may also like

Comments

Leave a reply