መመሪያዎች

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመንግስት በጀት ለሚሸፈኑ ወጪዎች የክፍያ ተመን መመሪያ

መመሪያዎች/ MIRH/ 11 ሐምሌ 2014

በ የገንዘብ ሚኒስቴር

የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰፋ ያለ መዋዕለ ንዋይ የሚፈስባቸው ግዙፍ የግንባታ ስራዎች የሚከናወንባቸው እና ለመማር ማስተማር፣ ለምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት በርካታ ወጪ የሚፈልጉ በባህሪያቸው ከሌሎች ሴክተሮች የተለዩ በመሆናቸውና ሴክተሩ በመንግስት የሚመደበውን ሀብትም ይሁን ተቋማት በራሳቸው የሚያመነጩት ሀብት ለተቋማት ተልእኮ መሳካት እንዲያውሉት አስቻይ የሆነ ግልጽ ሥርዓ እንዲኖራቸው በማስፈለጉ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመንግስት በጀት ለሚሸፈኑ ወጪዎች የክፍያ ተመን መመሪያ ቁጥር 56/2011 ወጥቶ በስራ ላይ መዋሉ ይታወቃል፡፡

ሆኖም በመመሪያው አፈጻጸም ባጋጠሙ  ችግሮችና በተለይም በ2003 ዓ/ም ከወጣው የመምህራን የትርፍ ሰዓት ክፍያ መመሪያ ጋር በተያያዘ ያጋጠመውን የአተገባበር ችግር በማስመልከት በተደጋጋሚ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እየተነሱ ስለሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጥያቄዎች በሚመልስ መልኩ ማስተካከል አስፈልጓል፤ እንዲሁም ተመን ያልወጣላቸው ክፍያዎችና ተመኖች በመኖራቸውና የተሻሻለ የአሠራር ሥርዓት ለመዘርጋት ያስችል ዘንድ ተመኖችና ተመን ያልወጣላቸው ክፍያዎች ትክክለኛ የአሠራር ሥርዓት ለመፍጠር እና የነበረውን የአሠራር ክፍተት ለመዝጋት ይህንን መመሪያ ማውጣት አስፈልጓል፡፡

በመሆኑም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመማር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በተቋም አመራርና አስተዳደር፣ እንዲሁም የመማር ማስተማሩን ሂደት በተግባር ትምህርት ለሚያግዙ የቴክኒክ ረዳትነት ስራዎች ከጫና በላይ እና ከመደበኛው ስራ ውጪ ለተከናወኑ ተግባራት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ተመን በወጥነት በማዕከል በማዘጋጀት የሚከፈሉ ክፍያዎች ሕጋዊ መሰረት እንዲኖራቸው በማድረግ የህዝብና የመንግስት ሃብት አጠቃቀም ውጤታማነት ለማስጠበቅ ይህ መመሪያ ወጥቷል፡፡

 

መመሪያውን ለማንበብ፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመንግስት በጀት ለሚሸፈኑት ወጪዎች የክፍያ ተመን መመሪያ

 

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የችሎት ስርዓት መመሪያ

Previous article

የተሻሻለ የቤቶች እና ይዞታዎች አስተዳደር መመሪያ

Next article

You may also like

Comments

Leave a reply