MIRH/ባህር ዳር/የካቲት 9፣ 2015
የኢትዮጵያ ናሽናል ሚዲያ ሳፖርት (ENMS) ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ሥነ-ተግባቦት ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር (Media, Information and Research Hub-MIRH) የመረጃ ቋት ምንነት፣ አጠቃቀም፣ የጽሑፍ ተሳትፎ እና ሌሎች እድሎችን በተመለከተ ከትምህርት ክፍሉ መምህራን እና ተማሪዎች ጋር ሰፊ ገለጻና ውይይት ተደርጓል፡፡
ገለጻውን የሰጡት የኢትዮጵያ ናሽናል ሚዲያ ሳፖርት (ENMS) መሥራች እና ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ዓለሙ ሲሆኑ የትምህርት ክፍሉ ተማሪዎች በሚራህ የመረጃ ቋት ስለሚያገኙት ጥቅም፣ የበጎ ፈቃድ ተሳትፎ፣ ልዩ ልዩ ጽሑፎችን አስመልክቶ ሰፊ ገለጻና ውይይት ሰጥተዋል፡፡
የትምህርት ክፍሉ ተማሪዎች በበኩላቸው ስለሚራህ MIRH የመረጃ ቋት አጠቃቀም የተደረገው ገለጻ እንዳስደሰታቸው እና ወደ ፊት በመረጃ ቋቱ ልዩ ልዩ ጽሑፎችን ለማበርከት ፈቃደኛ መሆናቸውን አንዳንድ ተማሪዎች በጥያቄና መልስ ውይይቱ ላይ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ናሽናል ሚዲያ ሳፖርት (ENMS) የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ የጋዜጠኝነት እና ተግባቦት ትምህርት ክፍሉ ሓላፊ አቶ ሰሎሞን ሙሉን ጨምሮ እና ሌሎች አስተባባሪዎችን ስላደረጉት ትብብር ምስጋና ያቀርባል፡፡





Comments