የግል መገናኛ ብዙሃን ፕሮፋይል / MIRH/ 30 ሰኔ 2014

ስብስብ መቅደስ ደምስ

ሪፖርተር በአማርኛ ቋንቋ በሳምንት ሁለት ጊዜ ረቡዕና እሑድ የሚወጣ በሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ሴንተር የሚዘጋጅ የግል ጋዜጣ ነው፡፡ ጋዜጣው “ዘ ሪፖርተር” በሚል ስያሜ በየሳምንቱ ቅዳሜ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚወጣ መንትያ አለው፡፡ ሁለቱም ጋዜጦች www.ethiopianreporter.com  (ኢትዮጵያን ሪፖርተር) በተባለ ድረገጽ ለአንባብያን ተደራሽ ናቸው፡፡

ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ሴንተር የተመሰረተው በ1987 ዓ.ም. ነበር፡፡ የድርጅቱ ባለቤት አቶ አማረ አረጋዊ የጋዜጣው አመሠራረት በኢትዮጵያ ነጻ መገናኛ ብዙሀን ተፈጥረው ለማየት የነበረውን ህልም እውን ከማድረግ ፍላጎቱና ተግባሩ ጋር እንደሚያያዝ ይናገራል፡፡

ሪፖርተር የተጀመረው በአንድ ቋንቋ ብቻ ነበር፡፡ የአማርኛው እትም ምስረታ ከእንግሊዝኛው ሪፖርተር ይቀድማል፡፡ ጋዜጣው ለመጀመሪያ ጊዜ በብርሀንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በ1987 ታትሞ ወደ ስርጭት ሲገባ ሳምንታዊ ነበር፡፡ ከህዝቡ ያገኘው ተቀባይነትም በወቅቱ ከፍተኛ የንባብ ፍላጎት እንደነበር ጠቁሟል፡፡ የነበረውን የበረታ የማንበብ ፍላጎት ለማርካት ሲባል ብዙም ሳይቆይ የአማርኛው ሪፖርተር በሳምንት ሁለት ጊዜ መታተም ጀመረ፡፡ ሥርጭቱም በመላ አገሪቱ ለመስፋፋት በቃ፡፡

የእንግሊዝኛው ዘ ሪፖርተር ለመጀመሪያ ጊዜ የአማርኛ እኩያው በተጀመረ በዓመቱ ወጣ፡፡ የውጭ አገር አንባቢያንን ተደራሽ የማድረግ ፍላጎት ለእንግሊዘኛው ኅትመት መጀመር ዋና ምክንያት ነበር፡፡ ስለሆነም ኤምባሲዎች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማትና የውጭ ዜጎች የሚያዘወትሩባቸው እንደ ባንክ ያሉ የስራ አካባቢዎች የጋዜጣው መዳረሻዎች ሆኑ፡፡

በሁለቱ ቋንቋዎች የሚዘጋጀው ሪፖርተር በድረ-ገጹ በመላው ዓለም ለሚገኙ አንባብያኑ ተደራሽ ነው፡፡ ድረ-ገጹ ለአንባብያን አስተያየቶች ሰፊ ስፍራ ሲሰጥ ቆይቷል አሁንም በተመሳሳይ፡፡

ሪፖርተር መጽሔት

ሪፖርተር ጋዜጣ ሥራ ከጀመረ ከአምስት ዓመታት በኋላ በ1993 ዓ.ም. “ዘ ሪፖርተር ማጋዚን” የተሰኘ መጽሔት ገበያውን ተቀላቀለ፡፡ መጽሔቱ በአማርኛና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች የሚታተም በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ባህልና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ወርሀዊ ህትመት ነበር፡፡ መጽሄቱ ለዓመታት በገበያ ላይ ከቆየ በኋላ በዓለም አቀፉ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝና በህትመት ዋጋ መጨመር ምክንያት በ2012 ዓ.ም. ከህትመት ውጭ ሆኗል፡፡ ቀደም ሲልም በተመሳሳይ በህትመት ዋጋ መናር ምክኒያት ህትመት አቋርጦ ነበር፡፡ በ2014 የድርጅቱ ሠራተኞች ብዛት 120 ነው፡፡

 

ምንጭ

www.thereporterethiopia.com

የመገናኛ ብዙሀን ጥናቶች

አማረ አረጋዊ፡ ሦስት ዓስርታት ዓመታትን የተሻገረ ስኬታማ የጋዜጠኝነት ሙያዊ ጉዞ

Previous article

ስለ ሞባይል ጋዜጠኝነት ማወቅ ያለብን

Next article

You may also like

Comments

Leave a reply