መመሪያዎች

ለሚዲያ ተቋማት የችሎት ክትትል መመሪያ

መመሪያዎች/ MIRH/ 12 ሚያዚያ 2022

በኢትዮጵየ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ታተመ

የኢትዮጵየ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ማን ነው?

የኢትዮጵየ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት መጋቢት 16 ቀን 2018 የተመዘገበ የ17 ሀገር በቀል የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ጥምረት ሲሆን፣ በምዝገባ ቁጥር 3932፣ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት ምዝገባውን አድሶ የሚንቀሳቀስ አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ነው፡፡ ኢሰመድህ በሀገሪቱ ውስጥ በዲሞክራሲ እና በሰብዓዊ መብቶች እንዲሁም በሰላም ግንባታ ውስጥ በመሳተፍ፣ ሰብዓዊ መብት ላይ ለሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ማህበር ነው።

ህብረቱ ሚዲያዎች ጋዜጠኞች የፍርድ ቤት ጉዳዮችን እንዲከታተሉ፣ እንዲመዘግቡ እና ሪፖርት እንዲያደርጉ እና በዳኝነትና በፍትህ ስርአቱ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን ለህዝቡ በማሳወቅ እና የህዝቡን ግንዛቤ በፍትህ ስርአቱ ላይ ለማሳደግ እንዲሁም የዜጎች የመረጃ ተደራሽነትን በተከታታይ እና በጥራት ለማሳደግ ይሰራል። ኢሰመድህ የFeteh (Justice) Activity – USAID ይህንን ማኑዋል በ4 (አራት) ቋንቋዎች እንዲተረጎምና ለህትመት እንዲበቃ ላደረጉት የገንዘብ ድጋፍ ምስጋነውን ያቀርባል፡፡

ጥቂት ስለማኑዋሉ

ይህ የፍርድ ቤትሂደት ዘገባ መመሪያ በዋነኝነት የተዘጋጀው የወንጀል ጉዳዮችን ለመዘገብ ፍላጎት ላላቸው ጋዜጠኞች እና ወይም የሚዲያ ተቋማት ሲሆን ዋና ዓላማውም መረጃ የማግኘት መብትን ለማስፋፋት እንዲሁም ፍትሃዊ የሆነ የፍርድ ቤት ስርአትን ለማስተዋወቅ ሲባል ነሐሴ 2013 ዓ.ም ታትሟል። ማኑዋሉ በወንጀል ሂደቶች ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉና የሚውሉ የሕግ ቃላትን ለፍርድ ቤት ሂደት ዘጋቢዎች ለማሳወቅ ይሞክራል፣እንዲሁም በፍርድ ቤት ዘገባ ውስጥ መከተል ስላሉባቸው ዘዴዎች ምክሮችን ይሰጣል። ይህም ሶስት ዓላማዎችን ይዞ ሲሆን እነርሱም፡-

  1. ሕግን አለማወቅ ከተጠያቂነት ሰለማያድን የሚዲያ ተቋሟትና ጋዜጠኞች ሕጋዊ መስፈርቶችን እንዲያከብሩና እንዲሁም አቅማቸውን በመጨመር በሕዝብ ዘንድ ያላቸውን ተዓማኒነትና ተቀባይነት ለማሻሻል ይረዳቸዋል።
  2. ህብረተሰቡ በፍርድ ቤት ጉዳዮች ላይ ትክክለኛና ሚዛናዊ ዘገባ በቋሚነት እንዲያገኝ ይረዳዋል።
  3. በፍትህ አካላት ላይ የህዝብ አመኔታን በማሳደግ ፍርድ ቤቶችን ቀስ በቀስ ለሚዲያ ክፍት በመሆን ከህዝብ ጋር የሚያደርጉትን ግንኙነትም ለማጠንከር ይረዳል። እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃንና የሰብዓዊ መብት ማኅበራት በፍርድ ቤት ሂደትና በችሎት ክትትል ላይ ተባብረው እንዲሰሩ የሚያግዝ ሲሆን በተለይም የሲቪል ማህበራት የችሎት ክትትል ሪፖርቶች ለፍርድ ቤት ሂደት ዘጋቢዎች ለሚሰሯቸው ታሪኮች አጋዥ ይሆናሉ።

ሙሉውን ለማንበብ የሚከተለውን ተያያዥ ልጥፍ ተጭነው ይክፈቱት

በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት የቴሌቭዥን ጋዜጠኛ

Previous article

ጋዜጠኛ እሌኒ መኩሪያ

Next article

You may also like

Comments

Leave a reply