ሚራህ (MIRH) ምንድን ነው?

ዲጂታል ምርምር ቋት

ሚራህ በቀጥታ ከእንግሊዘኛው ሥያሜ የተወሰደ ምሕጻረ-ቃል ሲሆን፤ የሚዲያ፣ ኢንፎርሜሽን እና ምርምር ቋት (Media Information and Research Hub-MIRH) ማለት ነው።

ይህ ሚዲያ የዲጂታል ማዕከል የሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙኀን ታሪክ፣ መረጃ፣ እድገት፣ ልዩ ልዩ የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን የጥናት ውጤቶች፣ የጋዜጠኞች ግለ-ታሪክ፣ የሙያ ልምዶች፣ የመገናኛ ብዙኀንና ጋዜጠኝነት ሙያዊ ማብራሪያ ሰነዶች እና ሌሎች ኹነኛ መረጃዎችን በአንድ ቦታ፤ በአንድ ጊዜ የሚገኙበት የመረጃ ቋት ነው፡፡

ሚራህ (MIRH) ከፎዮ የሚዲያ ማዕከል (Fojo-IMS በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ ናሽናል ሚዲያ ሳፖርት (ENMS) እየተተገበረ ያለ ፕሮጀክት ሲሆን የኢትዮጵያ ሚዲያ ካውንስል (Ethiopian Media Council)፣ የኢትዮጵያ ሴት የሚዲያ ሙያተኞች ማኅበር (Ethiopian Media Women Association - EMWA)፣ የኢትዮጵያ አርታኢያን ማኅበር (Editors Guild - EG)፣ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ራዲዮ አሠራጮች ማኅበር (Ethiopian Community Radio Broadcaster Association - ECRBA) እና የኢትዮጵያ ብሮካስተሮች ማኅበር (Association of Ethiopian Broadcasters - AEB) አብረውት ይሠራሉ፡፡